የዳግማዊ አጼ ቴዎድሮስ የሕይወታቸው መጨረሻ ሰዓት እና የመቅደላ ዝርፊያ

ይህ ታሪክ፣ በ1874 [1866 ዓ.ም]  ሄንሪ ኤም. እስታንሊ የተባለው የኒውዮርክ  ሄራልድ ጋዜጣ ተቀጣሪ  እንደ አውሮፖ አቆጣጠር በ1868 በጄኔራል ሮበርት ናፕዬር የተመራው የእንግሊዝ ጦር ጋር ወደ ኢትዮጵያ  በመጓዝ ያከናወነውን “ኮማሲ እና መቅደላ” በተሰኘው የሚመስጥ መጽሐፉ የመዘገበው ነው። ይህ አጭር ጽሑፍም የተጻፈው የንጉሡን ሕይወት ማለፍ ተከትሎ እስታንሊ በገጽ  449-464 ያሰፈረውን ሀተታ ማስረጃ  መሰረት በማድረግ ነው። በተጨማሪም በእውን ያያቸውን ከመቅደላ የተዘረፉትን ቅርሶች ገጽ 454-462 በዝርዝር ያስቀምጣል። የእንግሊዝ ጦር ወደ ኢትዮጵያ የዘመተበት ምክንያት ንጉሡ ለንግሥት ቪክቶሪያ የሁለቱ ሃገራት ወዳጅነት መመስረት እና መጠናከር በተመለከተ ለጻፉላቸው ደብዳቤ መልስ ስለተነፈጋቸው፣ በአጸፋው ያሰሯቸውን የእንግሊዝ መልክተኞች ከእስር ለማስፈታት መሆኑ ሊታወስ ይገባል።

  ‘አኽ፡ሹማዊት ሌሊት፥’                                                         

`አኽ፡ሹም`፥ጥንታዊ፥የ፡`ሳባዊ`፡ሥልጣኔ፡እንደነበራት፡እንጂ፥`ጥንታዊ~ሌሊት`፡እንደ፡አላት፥እስከ፡ዛሬ፡ድረስ፤ፈጽሞ፡ አላውቅም፡ነበር። ብፁዕነታቸው፥ንቡረ~ዕዱ፤የኣጎቴ፡ኣጎት፡ናቸው፥ በብርቱ፥የኅሊና፡ተጽዕኖ፡በሚያሳድር፡ደብዳቤአቸው፥በ፡አጣዳፊ፥ወደ፡`ኣኽ፡ሹም`፡መጥቶ፡እንዲጎበኛቸው፡ስለጠሩት፥ ደብዳቤው፡በደረሰው፡ሠልሥት፥ከ፡ኣሥመራ፡ተነስተን፡የገሠገሥነው።ኣጎቴ፥የ፡ኣሥመራ፡ማዘጋጃ፡ቤት፡ባለ፡ሥልጣን፡ሆኖ፡ከተሾመ፡ቆየ።እኔም፤ለክረምቱ፤የትምህርት፡ቤታችን፡መዘጋት፥ለእረፍት፤ ወደ፡እርሱ፡ዘንድ፡እንድመጣ፡ስለ፡ጠራኝ፤ኣባቴ፤በፍጹም፡ደስታ፤ኣውቶቡስ፡ኣሳፍሮ፡ላከኝ።

`ዔርታ~ዓሌ`፡~በእንተ፡ነገረ፥`ድንቂቱ`

“`ዔርታ፡ዓሌ፥ወበእንተ፡ነገራ፡ለ`ድንቂቱ`ተረክ ጭብጡ ዕውን ላይ የተመሠረተ ታሪክ ነው” ጃህእርሥዎ፡ሞትባይኖር፡ኪሩብ፡ዔል`፡~ በሚል መጠሪያ ለመጀመሪያ ጊዜ የምናትምለትን ይህን “ዔርታዓሌ ወበእንተ ነገራ ለድንቂቱ” በሚል ርዕስ ባቀረበው ትርክት እንዲታወቅ ቢፈልግም፣ በተለምዶ ስሙ “ጃርሶ ኪሩቤል”ተብሎ የሚታወቀው ይኸው ደራሲና ፀሐፊ በኪነ~ጥበብ ሙያ እና በ( ዔዞቴሪክ~ሳይንስ)ኅቡዕ የነገረ-ሰብ ጥናት እና ምርምር ላይ የተሰማራ ሰው ነው።

ሊቀ ሊቃውንት ጌታቸው ኀይሌ (1931-2021)

ስለሊቀ ሊቃውንት ጌታቸው ኅይሌ በምናነሳበት ጊዜ በተደጋጋሚ የተገለጠውን ታሪካቸውን ለመድገም ሳይሆን በተለይ ለሰምና ወርቅ ሁለ- ገብ የጥናትና የምርምር መጽሔት ያደረጉትን አስተዋጽዖ ከግል ታሪካቸው እንደ አንድ ምዕራፍ አድርገን ለማስተዋወቅ ከሚል ዓላማ ተነስተን ነው። በቅድሚያ ግን የመጽሔታችን አዘጋጆች ለሊቀ ሊቃውንት ጌታቸው ኅይሌ ያለንን አድናቆት በአንክሮ መግለጥ እንፈልጋለን፤ የመጽሔቱ ባለውለታ ናቸውና።

የዐፄ ካሌብ ወይም የቅዱስ ኤልስባን* ገድል

ዐፄ  ኢዛና  ሃሌን ንጉሠ ነገሥት 
ዘኢትዮጵያ ተብሎ አስር ዓመት 
ከገዛ በኋላ ከልጆቹ መሃል የአክሱም 
መኳንንት ካሌብን አነገሡ፤ 
ስመ ንግሡም ዳግማዊ 
ዓፄ እለ አጽብሃ ንጉሠ ነገሥት 
ዘኢትዮጵያ መሲሃ እግዚአብሔር 
ተብሎ በ483 ዓም ነገሠ።
ሰላሳ አምስት ዘመን ከገዛ በኋላ 
ሃይማኖቱ ኦሪታዊ የሆነ ዱኖባስ 
ፊንሐስ በናግራን [አሁን የመን 
ተብሎ በሚታወቀው] 
የክርስቲያኖች ቁጥር መብዛቱን 
አይቶ በግዛቱ ውስጥ የነበሩትን 
ከአራት ሺ በላይ ክርስቲያኖችን  
የገደለውን ንጉስ በማስወገዱ 
ይታወቃል። 

አቶ ዳምጤ አሰማኸኝ (አጭር የህይወት ታሪክ)

ከሁሉ አስቀድሜ የመጽሐፌን ርዕስ “የተዘጋው ምዕራፍ” ብዬ የሰየምኩበትን ምክንያት ልግለጽ። ምክንያቴ ቀላል ነው። ማንኛውም ሰው በራሱ እንጂ በአያትና በቅድመ አያቶች ጥፋት መቅቀጣት እንደሌለበት አምናለሁ። ያ፥ ለኔ የተዘጋ
ምዕራፍ ነውና። ይህን ታሪክ የጻፍኩበት የአባቶቻችንን ስህተት እንዳንደግም፥ ያለሙትን ደግሞ እንድናዳብር እንጂ “አያትህ አያቴን በድሎታልና ብድሩን በአንተ ላይ መመለስ አለብኝ” እየተባባልን እርስ በርሳችን ስንናቆር እንድንኖር አይደለም። ከዓለም ሕዝብ ሁሉ ወደሗላ ያስቀረን ይሄው ተከፍሎ የማያልቅ የበቀል ዕዳ ይመስለኛል። ለዚህ ነው ያ የበቀል ምዕራፍ እንዲዘጋ የፈለግሁት ምጽሐፉንም “የተዘጋው ምዕራፍ” ያልኩት።

ETHIOPIA: Nile, Renaissance Dam and Political Issues (June 2020) ስለህዳሴ ግድብ እና አባይ ወንዝ እንዲሁም ስለኢትዮጵያ፣ ሱዳን እና ግብፅ፣ ስለተፈጠረውም የፖለቲካ ቀውስ በሚመለከት ተመዝግበው የተገኙ የዜና ፣የጥናት ጽሑፎችና ሰነዶች ዝርዝር (ሰኔ 2012)፡፡

ይህ መዘርዝር ኢትዮጵያ ልትሰራው ባቀደችው እና በመተግበርም ላይ ባለው የህዳሴ ግድብ ዙሪያ በኢትዮጵያ፣ ሱዳን እና ግብፅ መካከል የተለያዩ ውይይቶች፣ ስምምነቶችና የሃሳብ ልዩነቶችም ተንፀባርቀዋል:: በመገንባት ላይ ባለው ግድብ የተነሳውን የፖለቲካ ጥያቄ፣ በውሃ ፖለቲካ ዙሪያ የቀርቡ ጥናቶችን ያጠናቀረ ዝርዝር እንዲሆን ጥረት ተደርጓል። የተሟላም ባይሆን በቪዲዮና በመጻሕፍት ሳቢያ የቀረቡ ጥናቶችንና ትችቶችን ጨምረናል። ይህ ጥረት በዚህ የሚገደብ ብቻ ሳይሆን አዳዲስ ውጤቶችን እየጨመረ  የሚቀጥል መዘርዝር እንዲሆን እቅድ አለን።

ፕሮፌሰር ሰይፉ በላይ (1951 – 2019)

ፕሮፌሰር ሰይፉ በላይና እኔ የተዋወቅነው እኔ የሐዋርድ ዩኒቨርሲቲ ተማሪና  የቤተ መጻሕፍቱ ሠራተኛ እያለሁ ነበር። እርሱ በዚያ ጊዜ የሳይንስ ፋክልቲ ተማሪ ነበር። ከተዋወቅን በጥቂት ጊዜ ውስጥ ቀደም ሲል  አውቀው ከነበረው አቶ ሙሉጌታ ከበደ  ጋር  ተቀናጅተን  አንድ  መጽሔት  እንድናቋቁም  ባቀረብኩላቸው ሃሳብ ላይ በመስማማታቸው በውይይት ሰምና ወርቅ ሁለገብ የጥናትና የምርምር መጽሔት በሚል ርእስ መጽሔት የማቋቋሙንና  በተግባር የመግለጹን እርምጃ   ተያያዝነው። እኔ የመጽሔቱ ዋና አዘጋጅ እንድሆን፣  ፕሮፌሰር ሰይፉና አቶ ሙሉጌታ ደግሞ የአዘጋጅው ቦርድ አባላት በመሆን አብረውኝ ሊሰሩ ተስማማን። የመጀመሪያውን እትም በምናዘጋጅበት ጊዜ እንደስምምነታችን በሁሉም የእውቀት ዘርፍ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን ያሉበትን ደረጃ በመገምገም እንድንጀምር የሚል ሃሳብ ስለነበረ ፕሮፌሰር ሰይፉ በሳይንስና ቴክኖሎጂ ያለውን ድርሻ በሚገባ ሰርቶ አቅርቦልናል። ከዚህም የመንደርደሪያ ጥራዝ በኋላ ፕሮፌሰር ሰይፉ በላይ በቀጣዩ ጥራዝ ላይ ማለትም ጥር 1979 ዓ.ም በታተመው እትም ላይ “የፕላስቲክ ኪነ ጥበብ” በሚል ርእስ ላይ ሰርቷል፤  ሰኔ 1979 ዓ.ም በታተመው ላይ ደግሞ “ጥንታዊ የብረት ቴክኖሎጂ በኢትዮጵያ” በሚል ርእስ አንድ መልካም ጽሑፍ ለአንባቢያን አቅርቧል። በመጨረሻም “የኢትዮጵያውያን የሳይንስ ሙያተኞች ድርጅት” በሚል አንድ ተጨማሪ ጽሑፍ ጥር 1981 ዓ.ም በወጣው እትም ላይ አቅርቧል። ፕሮፌሰር ሰይፉ በላይ ከሐዋርድ ዩኒቨርሲቲ በባዮቴክኖሎጂ ከፍተኛ ድግሪ ከተቀበለ በኋላ፥   በአሜሪካ መንግስት መሥሪያ ቤቶች (በዋልተር ሪድስና ኤን አይ ኤች – Walter…

የኢትዮጵያውያን ገዳምና ተማሪ-ቤት በቫቲካን፤ ግርማይ ተስፋጊዮርጊስ፤ ሰሜን አሜሪካ (ጥር 2012 ዓም)

ኢትዮጵያውያን ነጋድያን (ፕልግርምስ) ከአስራ አምስተኛ ክፍለዘመን ጀምረው የቅዱስ ጴጥሮስና የቅዱስ ጳውሎስ መቃብር ለመሳለም ወደ ሮም ይሄዱ እንድነበረ በቫቲካን መዛግብትና በኣንዳኣንድ የታሪክ ጸሓፊዎች ሰነዶች ተጽፎ ይገኛል። የሮም ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ለነዚህ ነጋድያን በቫቲካን ውስጥ የሚገኝ የትልቁ ቅዱስ ኢስጢፋኖስ ገዳም የሚባል ጥንታዊ ቤተክርስቲያን ከነ እንግዳ መኖርያ ቤት ሰጡዋቸው። ይህ ቤተክርስቲያን ለኢትዮጵያውያን ከተበረከተ በኋላ Santo Stefano Dei Mori “የቀይ ዳማዎች ቅዱስ ኢስጢፋኖስ” ተባለ። ከዛን ጊዜ ጀምሮ ይህ ቦታና ገዳም በኢየሩሳሌም በኩል ወደ ሮም ይሄዱ የነበሩ ኢትዮጵያውያን መነኮሳት ንብረት ሆኑ። መነኵሴዎቹ ከየትኞች የኢትዮጵያ ገዳሞች ይመጡ እንደነበረ ሁሉ በቫቲካን መዛግብት ተጽፎ ይገኛል። ደብረ-ዳሞ፣ ደብረ-ሊባኖስ፣ ደብረ-ቢዘን ወዘተ ለምሳሌ ሊጠቀሱ ይችላሉ፡፡ ይህ ከፍ ያለ ክብርና ታሪክ ያላት ብቸኛ ኣንዲት ኮሌጅ በቫቲካን ውስጥ መኖር ለኢትዮጵያ ህዝብ ትልቅ ክብር ነው። ስለዚህም የኢትዮጵያ ታልላቅ ሰዎችና ባለስልጣናት ወደ አውሮጳ ሲሄዱ ይህችን ኮሌጅ ሳይጎበኙ አያልፉም ነበር። ለምሳሌ ቀዳማዊ ኃይለስላሴ ሁለት ጊዜ፣ (አልጋውራሽ እያሉ በ1924 እና ንጉሠ-ነገሥት እያሉ በ1970 ዓ ም) ፥ ልዕልት ተናኘ ወርቅና ልዑል አስፍሓ ወሰን በ1932 ዓ. ም. በቅርቡም ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በ2019 ወዘተ. ይገኙበታል።

ዘረ ያዕቆብና ገብረ ህይወት ባይከዳኝ፤ ሁለት የዘመናዊነት እሳቤዎች በኢትዮጵያ ፍልስፍና፤ በፋሲል መርአዊ፤ (ሌክቸረር ፤ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ፍልስፍና ት/ክፍል)

በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ የዘመናዊነት ሀሳብ ከአንድ ትውልድ ወደ ሌላ ትዉልድ፣ ከአንድ ዘመን ወደ ሌላው ዘመን እየተሸጋገረ ይሄዳል፡፡ ስለዚህም እያንዳንዱ ማህበረሰብ የበለጠ ዘመናዊና በለውጥ የሚያምን መሆኑን ለማሳየት ይሞክራል፡፡ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ የዘመናዊነት ሀሳብ መገለጫዎች በተፈጥሮ የተለያዩ ናቸው፡፡ ስለዚህም በስነጥበብ፣ በፍልስፍና፣ በማህበረሰብ ትችና ዘመናዊ ትምህርት ውስጥ የተለያዩ ሀሳቦች ተንፀባርቀው እናገኛለን፡፡

በፍልስፍና መስክ ኢትዮጵያዊው ፈላስፋ ዘረያዕቆብ፣ የባህልና የወግ አስተሳሰቦችን ትችት በማዳበር በማህበረሰቡ ውስጥ ምክንያታዊነትና ማህበረሰባዊ ፍትህ እንዲሰፍን “ሐተታ” የተሰኘ ስራውን ለማዳበር ሞክሯል፤ ከዚህ ጋር በተያያዘ ኢትዮጵያዊው ምሁር ነጋድራስ ገብረህይወት ባይከዳኝ የሀገር በቀል ጥበብንና ምዕራባዊ ስልጣኔን ያጣመረ የዕድገት ጐዳና ለመቀየስ ሲሞክር ነበር፡፡ በነዚህ ሙከራዎች ላይ ተመርኩዘን ዘመናዊነት የበለጠ በኢትዮጵያ ውስጥ እንዲዳብር ምክንያታዊ የሆነ ማህበረሰብ እንድያብብ ማድረግ  ያስፈልጋል፡፡