የጥናት ጽሑፎች/አስተያየት
ሰምና ወርቅ እነሆ ከ30 ዓመታት በፊት የተጀመረ የጥናትና የምርመር መጽሔት ሲሆን በኢትዮጵያ ላይ ትኩረት የሚያደርጉ በርካታ ጥናታዊ መጽሔቶችን ሲያትም ቆይቷል። ዛሬም፣ ከሃያ አምስት ዓመታት በኋላ፣ የቀድሞዎቹን እትሞች እና አዳዲስ ጥናታዊ ጽሑፎችን አካቶ በአዲስ መልኩ semenaworq.org ላይ ማቅረብ ጀምሯል።
እርስዎም በማንኛውም ርዕስ ላይ ያተኮረ የምርምር ጽሑፍ እንዲልኩልን በአክብሮት እንጠይቃለን። ጥናታዊ ጽሑፎቹ ማሟላት የሚጠበቅባቸው መስፈርት ወረድ ብሎ ስለሚገኝ ይህንን አሟልተው የሚገኙትን ጽሑፎች ብቻ ለማተም እንደምንገደድ ከወዲሁ እናሳውቃለን።