“ለመላው ዓለም የቀረበ የፊደል ገጸበረከት” (ተክለማርያም ኀይሌ)

“ፊደሎች ጥንት እንደተፈጠሩ በነባርነት ሊኖሩ አይችሉም። ወረታቸው ያልፍና ለዛቸውን ያጣሉ። በዚያን ጊዜ አንዳንድ ታታሪዎች ወይም ደርጅቶች እየተነሱ ክብደታቸውንና አስቸጋሪነታቸውን እየገመገሙ አጣጣላቸውም ሆነ ቅርፃቸው ለጽሕፈት እንዲያመችና ለትምህርት እንዲቀል ማሻሻያ አሳቦችን ያበረክቱላቸዋል።”

“የኢትዮጵያውያን የሳይንስ ሙያተኞች ድርጅት” (ሰይፉ በላይ)

“የዚህ ድርጅት ዋና ዓላማ በሳይንስና ቴክኖሎጂ ጥናትና ምርምር የሚያካሂድና የሚያቀናጅ ስለሚሆን በተለይም ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ የሳይንስ ምሁራን በውጭ ከሚገኘው ኢትዮጵያዊ የሳይንስ ሙያተኛ ጋር ተገናኝተው የጥናትና ምርምር ተለምዶ የሚለዋወጡበትና የሚረዳዱበትን መንገድ የሚፈልጉበት መንኮራኩር መሆን ነው።”

“የወባ በሽታን ስለማጥፋት የተደረገ ልማዳዊ ጥናት” (ዮሐንስ)

“ለወባ በሽታ ያገኘሁት የባህል መድኃኒት ከሌሎች የወባ በሽታ መድኃኒቶች ጋር ሲነጻጸር ፍቱን የሆነ ነው። ምክንያቱም ረቂቆች ሕዋሳትን በፍጥነት ለማጥፋት ችሎታ ስላለው እንዲሁም በጭስ ወይም በሲጋራ መልክ ተዘጋጅቶ በአወሳሰድ በቀላል መንገድ መጠቀም ስለሚቻል ነው።”