የባህል መድኃኒቶች በተለያዩ የዓለም ክፍሎች እና የመድኃኒት ዕፅዋት እንክብካቤ አስፈላጊነት በኢትዮጵያ -(በቅርብ ጊዜ ታትሞ ከወጣው የመጻሕፍት ስብስቦች የተቀዳ) -(ዶ/ር ፈቃዱ ፉላስ)

ኢትዮጵያ በርካታ የብዝሃ ህይወት ሀብቶች አሏት። የባህል መድኃኒት ዕፅዋት ቁጥራቸው እየመነመነ መሄድ፣ በተለይም የመድኃኒት ዕውቀት ያላቸው አረጋውያን ዕልፈተ-ሕይወት አሳሳቢ መሆኑን ኢትዮጵያውያን አጥኚዎች… ጠቁመዋል። ከዚህም ጋር ተያይዞ በልዩ ልዩ ምክንያቶች መላ ማህበረሰቦች ከጊዜ ወደ ጊዜ መፈናቀላቸው፣ የመድኃኒት አዋቂዎች በዕድሜ መግፋትና ወጣቱ ትውልድ ከአረጋውያኑ ለመማር ፈቃደኛ አለመሆኑ ይህን ጠቃሚ ባህል የማቆየቱና የማስተላለፉን ችግር አባብሶታል። የደን መራቆት ትልቅ ችግር አስከትሏል።