ፍልስፍናና ፈጠራ

ኢትዮጵያውያን የራሳቸው ፍልስፍና ሆነ የመፈላሰፊያና የፈጠራ ዘዴና ዘይቤ የላቸውም የሚል አስተሳሰብ ለብዙ ጊዜ ሲነገር የቆየ ነው። ብዙዎቻችን ይህንን አስተሳሰብ ያለምርምር አምነንበት ኖረናል። ይህ በኢትዮጵያውያን ላይ የተሰነዘረው አመለካከት ምንጩ የት እንደሆነ ማወቅ ባያዳግትም በተጨባጭ ለማሳየት የሚረዳንን የጀርመኑን ፈላስፋ የሔግልን ጽሑፍ እንጠቅሳለን። ሔግል ስለአፍሪቃውያን በጅምላ የሰጠው አስተያየት እንዲህ ይላል፤

ታሪክ በኢትዮጵያ

የምንነሳው ኢትዮጵያ በታሪኳ ጥንታዊነት መታወቋን ምርኩዝ በማድረግ ነው። ይህ ሲባል ግን ጥንታዊ ታሪኳ በጅምላ የሚያኮራ ነበር ከሚል ትምክት ለመነሳት አይደለም። ከዚህ ጥንታዊነት ጋር ተያይዞ ሲወርድ ሲዋረድ የመጣውን ባህልና ያሁኑ ትውልድ የወረሰውን ማንኛውንም ታሪክ መመልከት ይኖርብናል። የጥንትና የቅርቡ ታሪክ በሚነሳበት ጊዜ የምንማረው ምንድነው ከሚል ጥያቄ አንፃር መሆን ይኖርበታል። መጥፎውን መጥፎ፣ ጥሩውን ጥሩ ለማለት ግን ታሪክን የምናይበትና የምንመረምርበት መመልከቻ ዘዴ የግዴታ እንዲኖረን ሊያስፈልግ ነው።

ሳይንስና ቴክኖሎጂ

የአገራችን ሳይንቲስቶች ምንም እንኳን በቁጥራቸው ያነሱ ቢሆኑም በራሳቸው ላይ ጠንካራ እምነት እስካላቸው የሌላ ወገኖቻቸውንም ንቃትና ሕሊና መቀስቀስ እንደሚችሉ እምነት አለን። አውሮጳውያን አፍሪቃ ላይ ካደረሱት በደል አንዱ የራሳችን የሆነውን ባህልና ሕብረተሰብ እንድንንቅና በራሳችን እምነት አጥተን ለእነሱ የአእምሮ ባሪያዎች ሆነን እንድንኖር ማድረጋቸው ሲሆን ይህን አጥብቆ መዋጋቱ የኛ ፋንታ ነው። የራሳችንን ዕድገት በራሳችን እንድንወስን “ሰምና ወርቅ” ይህችን አምድ ከፍቷል።

ባህል ሥነጽሑፍና ኪነጥበብ

በኢትዮጵያ ከየብሔረሰቡ የሚፈልቁ ብዙ አሸብራቂና አስደሳች ትርጉም የሚሰጡ የባሕል ቅርሶች አሉ ። ብዙ ዓይነት ጣዕመ ዜማ ያላቸው የሙዚቃ መሳሪያዎችም ቁጥራቸው በርካታ ነው። ብሔራት የባህላቸውን ምንነት የሚገልጹባቸው የራሳቸው የሆነ የስእልና የቅርጻ ቅርጽ አቀራረጽ አሳሳልና ልዩ ልዩ ብልሃት ሞልቷል። ይህ ሁሉ አስደናቂ ነገር አብይ ቅርስ ስለሆነ ይህ ትውልድ የራሱ የሆነውን ቅርሳዊ ሃብት ኮርቶበት ለመጪው ትውልድ በቂ መሰረት ለማቆየት አካባቢውን አጥንቶና መርምሮ ማወቅና ማሳወቅ ማቆየት ይገባዋል።

ፖለቲካና ኢኮኖሚ

ፖለቲካና ኢኮኖሚን አስመልክቶ ስለኢትዮጵያ የሚደረግ ምርምር ጥናትና ትንተና አላማው በሀያኛው ክፍለ ዘመን የዚህች ሃገር ኢኮኖሚ እጅግ ማዘቅዘቅ ከምን ሁኔታና ምክንያት ጋር እንደሚያያዝ መፍትሄ ለማግኘት መሆን ይገባው ይሆናል ። በህገሪቱ ውስጥ ከብዙ ዘመናት ሲጥመለመል የቆየው የፖለቲካ ሂደት ከጊዜ ወደ ጊዜ አስከፊ ውጤት እያስከተለ መሄድ ሃገሪቷ ከነበረችበት አንጻራዊ መደላደል ወደባሰ አለመደላደል ማዘቅዘቁ የፖለቲካ ባህል እያደር እያደገ በመሄድ ፋንታ የተለያዩ ቅራኔዎች መፋፋምና በቅራኔው አፈታት ላይ የተወሰዱት እርምጃዎች ፣የተፈጠሩት ችግሮች …ወዘተ የእነዚህ ሁሉ ምክንያት በምርምር መልስ ማግኘት አለበት ።

የትምህርት አሰጣጥና አወራረስ

በአፍሪቃ ሀገሮች በተለይም በኢትዮጵያ ያለውን የኢኮኖሚና የልማት ሁኔታ ስንመለከት ከብዙ ዘመናት ጀምሮ ተስፋ የተጣለበት ትምህርት ለሃገሪቱ ብልጽግናን ለምን አላመጣም። ትምህርትስ በኢትዮጵያ ዕድገት ላይ የተጫወተው ሚና የቱን ያህል ነው፤ ነበርስ ብለን እንድንጠይቅና ጠለቅ ብለን እንድንመረምር ይጋብዛል ። ስለዚህ ጉዳይ ለአንባቢዎች ጽሁፍ ሊያበረክቱ ለሚሹ ሁሉ መንደርደሪያ እንዲሆን በማለት የሚከተሉትን ነጥቦች እናነሳለን ።