የታኅሳስ 1953 ዓ.ም ግርግር በከፊል – ከሻለቃ ያሬድ ቢተው – ዋሺንግተን ዲሲ፣ ሰሜን አሜሪካ – ጥቅምት 2017 ዓ.ም
በጽሁፉ ውስጥ የተካተቱት ቁምነገሮች የመጀመሪያ ደረጃ ምልከታ ምዝገባ ተብለው ከሚጠቀሱት የታሪክ ማጣቀሻ ማስረጃዎች ውስጥ የሚካተቱ ናቸው።
በስነ-ጽሁፍ አቀራረብ ረገድ በወቅቱ የነበረውን የጦማር አጻጻፍ ስልት አጉልቶ በማሳየት በዘመናት መካከል የተፈጠረውን የደብዳቤ እንዲሁም ታሪክ አዘጋገብ የእድገት ወይም ውድቀት ደረጃ አጉልቶ የሚያሳይ በመሆኑ ለስነጽሁፍ ተመራማሪዎች የሚሰጠው ፋይዳ ቀላል አይሆንም።
ከታሪክ አንጻር የወሰድነው እንደሆነ በወቅቱ የተሟላ ማስረጃ ያልተገኘላቸውን እውነታዎች ለህብረተሰባችንና ለታሪክ ተመራማሪዎች በመስጠቱ ረገድ የላቀ አስተዋጻኦ ይኖረዋል:: በዋናነትም የግለታሪክ ዘጋቢው በኩነቱ ወቅት እርምጃው በተወሰደባቸው ቀናት ውስጥ ተሳታፊ የነበሩ በመሆናቸው በአይናቸው የተመለከቱትን የዘገቡ በመሆኑ ከዚህ በፊት ኩነቱን አስመልክቶ የተጻፉ የጥናትና ምርምር ስራዎች ጉድለት በማሟላቱ ረገድ ፋይዳው የጎላ ነው።
የሰምና ወርቅ መጽሔት አዘጋጅዎች








