January 1990

ሥነጽሑፍ, ቁጥር 7

“ቅኔና ፅንሰ ሀሳቦቹ – ክፍል 1” (ፈንታሁን ጥሩነህ)

“በዚህ ጽሑፍ ቅኔ ለሥነ ጽሑፍ ያደረገውን አስተዋፅኦ በመጠኑ ለማስረዳትና የራሱ የሆነ የትችት አቀራረብ ዘዴ በመጠቀም የሥነጽሑፍ ደረጃ ከፍ እንዲል የሚያደርግ መሆኑን ጭምር ለማጤን ሙከራ እናደርጋለን።”

ቁጥር 7, ባህል

“ኢትዮጵያ ወዴት” (ተቀባ ሀብተወልድ)

“ኢትዮጵያ በፅኑ ችግር ላይ ናት። ኢትዮጵያን የገጠማት ችግር በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ ሁላችንንም የሚነካ ነው። ስለሆነም መፍትሔው የሁላችንንም ቀና አስተዋፅኦ ማድረግ ስለሚጠይቅ ችግሩን በሚገባ መረዳት ይገባል።”

ሥነጽሑፍ, ቁጥር 7

“የጨዋታ ትችት” [ግምገማ] (ዮናስ አድማሱ)

“መጽሐፉ ትእግሥትን ይጠይቃል፤ በገጽ ብዛት ዳጎስ በማለቱ አይደለም (“ፍቅር እስከ መቃብር” ይበልጣል፣ “አንድ ለናቱ” ይብሳል)። ለብዙዎቻችን አማርኛው እንግዳ ነው። የሚያስደነግጥ፣ ስለዚህም የሚያሸሽ የሚመሳስለው የዐረፍተ ነገሮቹ አሰካክና ባካባቢው ልዩ ዘየ ተታሸው የጨዋታ ዘይቤ ወይም ዚቅ ነው።”

Scroll to Top