የአቶ ሰይፉ መታፈሪያ የሥነግጥም መድብሎች የጥናት እና የምርምር ሥራዎች ።

ገጣሚ ሲቆጣ (ሰይፉ መታፈሪያ)፣
መጻፍ፣ መጻፍ አለኝ ማቅለም ወረቀት፣ ብእሬን ማስቆጣት ቀይ ደም ማስተፋት።

ዕውቁ ገጣሚ፣ መምህር እና የፎክሎር ባለሙያ ሰይፉ መታፈሪያ ፍሬው በርካታ ያገራችንን እና የአውሮጳን ቋንቋዎች አጥርተው የሚናገሩ እና ጠንቅቀው የሚያውቁ ልሳነ ብዙ ምሁርና ተመራማሪ ናቸው። በኢትዮጵያ እጅግ የተለየ የግጥም አጻጻፍ ስልትን ያስተዋወቁና ያስፋፉ ዕውቅ ገጣሚ ናቸው። እሳቸው እንደሚሉት የግጥማቸው የአጻጻፍ (ዓይነት) „በብዙ ረገድ ባህል-ከተል አይደለም። በዚህ ያጻጻፍ አዲስነት አስገዳጅነትም ስም ስላስፈለገው „ስንኝ አጠፍ ግጥም“ የሚል ስያሜ ሰጥተውታል። ላለፉት ሃምሳ ዓመታት በሀገራችን ቁጥራቸው በርካታ የሆኑ የፎክሎር እና የሥነ ጽሑፍ ተማሪዎችን እና ምሁራንን አፍርተዋል።