አቶ ዳምጤ አሰማኸኝ (አጭር የህይወት ታሪክ)

ከሁሉ አስቀድሜ የመጽሐፌን ርዕስ “የተዘጋው ምዕራፍ” ብዬ የሰየምኩበትን ምክንያት ልግለጽ። ምክንያቴ ቀላል ነው። ማንኛውም ሰው በራሱ እንጂ በአያትና በቅድመ አያቶች ጥፋት መቅቀጣት እንደሌለበት አምናለሁ። ያ፥ ለኔ የተዘጋ
ምዕራፍ ነውና። ይህን ታሪክ የጻፍኩበት የአባቶቻችንን ስህተት እንዳንደግም፥ ያለሙትን ደግሞ እንድናዳብር እንጂ “አያትህ አያቴን በድሎታልና ብድሩን በአንተ ላይ መመለስ አለብኝ” እየተባባልን እርስ በርሳችን ስንናቆር እንድንኖር አይደለም። ከዓለም ሕዝብ ሁሉ ወደሗላ ያስቀረን ይሄው ተከፍሎ የማያልቅ የበቀል ዕዳ ይመስለኛል። ለዚህ ነው ያ የበቀል ምዕራፍ እንዲዘጋ የፈለግሁት ምጽሐፉንም “የተዘጋው ምዕራፍ” ያልኩት።