ሥነጽሑፍ

ሥነጽሑፍ

መጽሐፈ ምሳሌ ዘጨዋ ተረት፤ እውሩና አንካሳው

ባንድ ከተማ ሽፍታ መጥቶ  ሰው ሁሉ ነፍሱን ለማዳን ሸሸ። ሁለት ሰዎች ቀሩ ይላሉ። እነርሱም እውርና አንካሳ ናቸው። እውሩም የሚመራው ፣ አንካሳውም የሚሸከመው አጥተው ተጨነቁ። ስለዚህ ተማከሩ። እውሩ አንካሳውን ተሸከመው፤ በእውሩ እግር በመፃጉዑ ዓይን እንደ አንድ ሰው ሆነው ሀገር ወዳለበት ደረሱና ነፍሳቸውን ከሞት አዳኑ። ሰው ሁሉ እንዲሁ በምክር ቢተባበር ደኅንነት ይሆንለታል።

ሥነጽሑፍ, ባህል

ስለ ባህል አንዳንድ ነጥቦች – የመነሻ ሀሳብ

ኢትዮጵያ የብዝሀ ብሄረሰቦችና ማህበረሰቦች ሀገር ናት፡፡ እነዚህ የኢትዮጵያ ብሄረሰቦችና ማህበረሰቦች አንደየአካባቢያቸው የተፈጥሮና የአየር ንብረት አንዲሁም በአንድ በኩል በተናጠል በሌላ በኩል ደግሞ እርስ በርስ ባደረጓቸው መስተጋብሮች የፈጠሯቸው ብዝሀ ባህላዊ እሴቶች አሏቸው፡፡ እነዚህ ብዝሀ ባህላዊ እሴቶች ለፈጠሯቸው የህብረተሰብ ክፍሎች እየሰጡት ካሉ ፖለቲካዊ ፣ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጠቀሜታዎች በዘለለ በአገር አቀፍ ደረጃ አንድ የፖለቲካ እንዲሁም ተደጋጋፊ የኢኮኖሚ ማህበረሰብ በመፍጠሩና ጠንካራ ሀገረ መንግስት በመገንባቱ ረገድ የበኩላቸውን የማይታለፍ ድርሻ እንደሚወጡ ይታመናል፡፡ በዚህ የባህል አምድ ስር ስለ ባህል በአጠቃላይ፤ የባህል ምንነት ጠቀሜታና አተገባበር ከኢትዮጵያ አጠቃላይ ብሄረሰቦችና ማህበረሰቦች እንዲሁም አለም አቀፍ ተሞክሮ አንጻር ሃሳቦችን እየሰደርን የምናቀርብ ይሆናል፡፡ ጽሁፉ ተከታታይነት ባለው መልክ የሚቀርብና ሁሎቹንም የባህል ዘውጎችና ዘርፎች የሚዳስስ ሲሆን፤ ለዛሬ የባህልን ትርጓሜ፤ አለም አቀፍና አገር አቀፍ አተያይ በማሳያነት በማቅረብ አሃዱ ብለናል።

ሥነጽሑፍ, ባህል

ሌስላውን ዘረፋ – አጭር የምርምር ማስታወሻ

ይህ አጭር ማስታወሻ የሴማዊ ቋንቋዎች ጥናት አባት ተብለው የሚታወቁት ዎልፍ ሌስላው (Wolf Leslau) በ1961 የዐማርኛ የገደል ማሚቶ ጥምር ቃላት የተሰኘውን መጣጥፋቸውን ለመቃኘትና እውቅና ለመስጠት በአቶ ዳናኤል አበራ ተዘጋጅቶ ቀርቦአል። ሌስላው በጥናቱ ላይ 80 ጥምር ቃላቶችን በመለየት በማሳያነትም እንደ አርቲ ቡርቲ …እንቶ ፈንቶ የሚሉትንና “ምንም ቁም ነገር የለውም… የማይረባ ነው…” ለማለት የሚጠቅሙትን ገልጸዋል። በአሁኑ ጊዜ ከእነዚህ 80 ጥምር ቃላት መካከል 25ቱ ጥቅም ላይ የዋሉ ሲሆኑ 11 ቃላትን አቅራቢው ጨምረዋል ። እነዚህ አስተጋቢ ቃላቶች ከ6 ሚሊዮን የአማርኛ ቃላት ጋር ተጣጥመው ተገኝተዋል።

ሀይማኖት, ሥነጽሑፍ, Uncategorized

ስለኢትዮጵያ፡ደራሲያን።

ጽሑፉ፡የፕሮፌሰር፡ታምራት፡አማኑኤል፡ነው። ፕሮፌሰር፡ታምራት፡ከሰማንያ፡ዓመታት፡በፊት፡በትምርትና፡ሥነጥበብ፡ሚኒስቴር፡አማካሪ፡ኾነው ይሠሩ፡ነበር። ነገር፡ግን፡በዚያን፡ጊዜ፡ፕሮፌሰር፡በመባል፡ፈንታ፡ሊቀማእምራን፡ይባሉ፡ነበር። ፕሮፌሰሩ ሲናገሩም :- “ባ፩ኛው፡ዘመን፡በዐማርኛ፡የተጻፈው፡ሥራ፡ እጅግ፡ጥቂት፡ነው።የተጻፈውም፡ላንዳንድ፡ነገሥታት ምስጋና፡ደራሲው፡ካልታወቀ፡የተገጠመ፡ቅኔ፡ነው። ቅኔውም፡በዘመናት፡ውስጥ፡አንድ፡ቋንቋ፡እንደምን፡ ኹኖ፡እየተለዋወጠ፡ለመኼዱ፡ዋና፡ምስክር፡ከመኾኑ በላይ፣በዚያ፡ዘመን፡የነገሥታቱ፡ሥልጣንና፡የተዘረጋበት፡የሰፊው፡አገር፡ኹኔታ፡እንዴት፡እንደነበረ፣ለታ ሪክና፡ለዦግራፊም፡ማስረጃ፡ለመኾን፡ይረዳል። ዐማርኛው፡ዛሬ፡ዘመን፡የማንናገርበትና፡የማንጽፈው፣ለማስተዋሉም፡የሚያስቸግረንና፡የሰዋስው፡አካኼድ፡የተለዋወጠ፡ብዙ፡ቃልና፡አገባብ፡አለበት። እርሱን፡የመሰለ፡ዐማርኛም፡በየዘመኑ፡እየተጻፈ፡ምናልባት፡እስከ፡ ፲፭፻፺፱-፲፮፻፯፡ደርሶ፡ ይኾናል።”

ሥነጽሑፍ, የሕይወት ታሪክ, ጥናትና ምርምር

የአቶ ሰይፉ መታፈሪያ የሥነግጥም መድብሎች የጥናት እና የምርምር ሥራዎች ።

ገጣሚ ሲቆጣ (ሰይፉ መታፈሪያ)፣
መጻፍ፣ መጻፍ አለኝ ማቅለም ወረቀት፣ ብእሬን ማስቆጣት ቀይ ደም ማስተፋት።

ዕውቁ ገጣሚ፣ መምህር እና የፎክሎር ባለሙያ ሰይፉ መታፈሪያ ፍሬው በርካታ ያገራችንን እና የአውሮጳን ቋንቋዎች አጥርተው የሚናገሩ እና ጠንቅቀው የሚያውቁ ልሳነ ብዙ ምሁርና ተመራማሪ ናቸው። በኢትዮጵያ እጅግ የተለየ የግጥም አጻጻፍ ስልትን ያስተዋወቁና ያስፋፉ ዕውቅ ገጣሚ ናቸው። እሳቸው እንደሚሉት የግጥማቸው የአጻጻፍ (ዓይነት) „በብዙ ረገድ ባህል-ከተል አይደለም። በዚህ ያጻጻፍ አዲስነት አስገዳጅነትም ስም ስላስፈለገው „ስንኝ አጠፍ ግጥም“ የሚል ስያሜ ሰጥተውታል። ላለፉት ሃምሳ ዓመታት በሀገራችን ቁጥራቸው በርካታ የሆኑ የፎክሎር እና የሥነ ጽሑፍ ተማሪዎችን እና ምሁራንን አፍርተዋል።

ሥነጽሑፍ, ታሪክ, ጥናትና ምርምር

አውሮጳ እና ኢትዮጵያ፤ አመራርና የሥልጣኔ ፖለቲካ

በዘመነ መሳፍንት ስድሳ አምስት ዓመት ሙሉ በማይረባ ምክንያት የተከፋፈለውን፣ የዘቀጠውን፣ የባለገውን ህዝባችንን ከወደቀበት መቀመቅ አውጥተው ኢትዮጵያን ወደጥንት ታላቅነቷ ለመመለስ የኢትዮጵያን ነገሥታት፣ መጀመሪያ አፄ ቴዎድሮስ፣ ቀጥሎ አፄ ዮሐንስ በኋላም አፄ ምኒልክ ያውሮጳን መንግሥታት ድጋፍና ወዳጅነት አጥብቀው ይፈልጉ፣ ይማጠኑ ነበር። አውሮጳውያን ግን የሚፈልጉት የኢትዮጵያን ውድቀቷን፣ ክፍፍሏን፣ ንብረቷንና መሬቷን እንጅ የሕዝቧን ነፃነትና ብልጽግና ስላልነበር በነዚህ ቅን ነገሥታቶች ላይ በየጊዜው ተደጋጋሚ አሳፋሪ ሸርና ተንኮል፣ ሴራና ተራ ማጭበርበር ይፈጽሙባቸው ነበር።

ሥነጽሑፍ, ባህል

መጽሐፈ ምሳሌ ዘጨዋ ተረት  

ይህ መጽሐፍ ያልታተመና በዩናይትድ ስቴትስ የኮንግሬስ ቤተመጻሕፍት ውስጥ በአፍሪካና በመካከለኛው ምሥራቅ ዋና ክፍልየኢትዮጵያና የኤርትራ ሃገራት የመጻሕፍት ክምችት ክፍል ውስጥከሌሎች ካልታተሙ የግእዝ፣ የአማርኛና የትግርኛ መጻሕፍት ጋርይገኛል። የተጻፈው በ1911 ዓ.ም ሲሆን ተረቶቹን በጽሑፍያሰፈረው የንጉሥ ወልደጊዮርጊስ አሽከር ነኝ የሚለው ነጋዴው አቶአበሩ የተባለ  የማጂ ከተማ ነዋሪ ሰው ነው። ይህን ያጠናቀረውንየጥንት ተረት መድብል ለወዳጁ  ለእንግሊዝ መንግሥት መኮንንለሜጀር አጥሒል [Major Athil] ሲያበረክት በመጽሐፉ ላይ ተጽፎእንደተገኘው፣ “ ይህን እያዩ እንዲያስታውሱኝ” ከሚል ማሳሰቢያ ጋርነበር። በዚህ መድብል ውስጥ በወረቀት ላይ ተጽፈው የተገኙተረቶች አስራ ሁለት ያህል ናቸው።

ሥነጽሑፍ

  ‘አኽ፡ሹማዊት ሌሊት፥’                                                         

`አኽ፡ሹም`፥ጥንታዊ፥የ፡`ሳባዊ`፡ሥልጣኔ፡እንደነበራት፡እንጂ፥`ጥንታዊ~ሌሊት`፡እንደ፡አላት፥እስከ፡ዛሬ፡ድረስ፤ፈጽሞ፡ አላውቅም፡ነበር። ብፁዕነታቸው፥ንቡረ~ዕዱ፤የኣጎቴ፡ኣጎት፡ናቸው፥ በብርቱ፥የኅሊና፡ተጽዕኖ፡በሚያሳድር፡ደብዳቤአቸው፥በ፡አጣዳፊ፥ወደ፡`ኣኽ፡ሹም`፡መጥቶ፡እንዲጎበኛቸው፡ስለጠሩት፥ ደብዳቤው፡በደረሰው፡ሠልሥት፥ከ፡ኣሥመራ፡ተነስተን፡የገሠገሥነው።ኣጎቴ፥የ፡ኣሥመራ፡ማዘጋጃ፡ቤት፡ባለ፡ሥልጣን፡ሆኖ፡ከተሾመ፡ቆየ።እኔም፤ለክረምቱ፤የትምህርት፡ቤታችን፡መዘጋት፥ለእረፍት፤ ወደ፡እርሱ፡ዘንድ፡እንድመጣ፡ስለ፡ጠራኝ፤ኣባቴ፤በፍጹም፡ደስታ፤ኣውቶቡስ፡ኣሳፍሮ፡ላከኝ።

ሥነጽሑፍ

የኢትዮጵያ ጊዜያዊ ሁኔታና የመንፈሳዊ ፖለቲካ ራዕይ ከፈንታሁን ጥሩነህ (ዋሺንግተን ዲ.ሲ)

ሰኔ ወር 2010 ዓ.ም ጀምሮ በኢትዮጵያ ምድር የሚካሄደው የለውጥ ነፋስ አዲስና አስገራሚ ነው። በእግዚአብሔር ማመን ተስፋ አስቆርጧቸው የነበሩ ሁሉ ተገርመው የዶክተር አቢይ አህመድ አሊ በፖለቲካው መስክ መነሳት ላይ “የእግዚአብሔር እጅ አለበት” እስኪሉ ድረስ ሁኔታው ማራኪ ሆኖ ይገኛል። በምዕራቡና በምሥራቁ ዓለም የፖለቲካ ንድፈ-ሃሳቦችና ጽንሰ-ሃሳቦች የተራቀቁ ኢትዮጵያውያን ምሁራን በሁኔታው በመደመም የሚሉት አጥተው ዝምታን የመረጡበት ጊዜ ነው። አንዳንድ ዜጎች ደግሞ ይህ ክስተት ጊዜያዊ ቅዠት እንጂ እውን አይደለም በማለት ያላቸውን ግራሞት ይገልጻሉ። እኔ በበኩሌ በዶክተር አህመድ አሊ የሚመራው አዲሱ ፖለቲካ ሲጠበቅ የነበረው የእግዚአብሔር ጣልቃ ገብነት ያስከተለው መሆኑን አምናለሁ። ይህ እምነቴ ደግሞ ይህን መጣጥፍ እንድጽፍ ምክንያት ሆኖኛል።

Scroll to Top