ኢትዮጵያ፤ የአባይ ወንዝ ባለቤትነትና ተጠቃሚነት ጥያቄ ፤ ኪዳኔ ዓለማየሁ ፤ መስከረም 2012

በጥንቱ ዘመን፤ የአባይ ወንዝ ዋናዋ ምንጭ ኢትዮጵያ መሆኗና ባለቤትነቱዋ ታውቆ፤ የግብጽ መሪዎች በየዓመቱ ለሚጎርፍላቸው ውሀ ይከፍሉ ነበር። በቅርቡ በየድረ-ገጹ በስፋት ከሚቀርቡት ሐተታዎች፣ ትችቶችና አስተያየቶች ውስጥ ሰፊ ስፍራ ይዞ የሚገኘው አንደኛው አርእስት ኢትዮጵያ ውስጥ በመገንባት ስላለው ታላቅ የአባይ ግድብ ነው። ስለ ግድቡ የተንጸባረቁት የተለያዩ አስተያየቶች እንዳሉ ሆነው የአባይ ወንዝ ባለቤትነት የማን እንደ ሆነና በጋራ ተጠቃሚነት ዙርያ ውሱን በሆነ መንገድ ተነካ እንጂ በጥልቀት በተከናወነ ምርመራና በዓለም-አቀፍ ሕግ በተመሠረተ አስተማማኝ ማስረጃ የተደገፈ ጽሑፍ አልቀረበም። የዚች ጦማር ዓላማም ኢትዮጵያ ከሱዳንና ከግብጽ ጋር እንዲሁም ከሌሎች የአባይ ተፋሰስ ሀገሮች ጋር  በምታከናውናቸው ውሎች ያሁኑንና የመጪውን ትውልድ እንዲሁም የሌሎች ሀገሮችን መብት በሚጠብቅ ሥልት መጠቀሟን እንድታረጋግጥ ተገቢውን ቅድመ-ዝግጅትና ጥንቃቄ እንድታደርግ ለማሳሰብ ነው።

ወይዘሮ ሲልቪያ ፓንከርስት እንግሊዛዊቷ የኢትዮጵያ ጀግና፤ ኪዳኔ ዓለማየሁ ፤ ሰኔ 18 ቀን 2011 ዓ/ም

ይህ አጭር ጽሑፍ (1) የሚያተኩረው፤ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን፤ ወለተ ክርስቶስ ተብላ በተሰየመችው፤ የዓለም ስሟ ሲልቪያ ፓንከርስት በሆነው፤ ኢትዮጵያ በፋሺሽቶች በተወረረችበት ጊዜ፤ ከዚያም በሁዋላ ሌሎች ቅኝ ገዢዎች ሊቀራመቷት በቋመጡበት ዘመን በሚያስደንቅ ጀግንነት 20 ዓመት ሙሉ በታገለችው፤ በተከበረች፤ ወይዘሮ የሕይወት ታሪክ ላይ ነው።

ሲልቪያ ፓንከርስት፤ እ.ኤ.አ በ1882 እንግሊዝ ሐገር ተወልዳ፤ ከዚህ ዓለም በሞት የተለየችው፤ እ.ኤ.አ መስከረም 27 ቀን 1960 አዲስ አበባ ነበር። አስከሬኗ የተቀበረውም፤ ወለተ ክርስቶስ ተሰኝታ፤ እንደ ሌሎች ታላላቅ አርበኞች፤ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ፤ ልዑል አልጋ ወራሽ አስፋ ወሰንና ሌሎች ክቡራን በተገኙበት በቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን ነበር። የ50ኛው ዓመት መታሰቢያዋ መስከረም 17 ቀን 2003 ዓ/ም በቅድስት ሥላሴ ቤ/ክ ተከብሯል።

ቀኛዝማች አባ ናዳ፤ (ቀኛዝማች ድልነሣሁ ጠንፉ) የኢትዮጵያ ጀግናና ዲፕሎማት ከኪዳኔ ዓለማየሁ

አባ ናዳ ከቅርብ ዘመዳቸው ከልዑል ራስ መኰንን ወልደሚካኤል ጋር በመዝመት ሐረርጌ በቅኝ ገዥዎች እንዳትያዝ ካደረጉት ጀግኖች አንዱ ናቸው። ዓረቦች፣ እንግሊዞች ፣ ፈረንሳዮችና ኢጣልያኖች ሐረርጌን ለመያዝ አሰፍስፈው በነበረበት ጊዜ በአጼ ምኒልክ ብልሕና ፈጣን እርምጃና አመራር በነራስ መኰንንና አባ ናዳ ቆራጥነት ሐረርጌን ለማዳን ችለዋል። አባ ናዳ መኖሪያቸውን ጃርሶ ጎሮ አድርገው በልዑል ራስ መኰንን መሪነት ሐረርጌ ከሌላው የኢትዮጵያ ክፍለ-ግዛት ጋር የነበራት ትስስር እንዲጠናከር አድርገዋል። አባ ናዳን አስደናቂ የሚያደርጋቸው ሌላው ከፍ ያለ ቁምነገር በ1889 ዓ/ም ከራስ መኰንን ጋር ኢጣልያ ተጉዘው ከልዑካኑ ጋር በመሆን በጊዜው ከነበሩት ከንጉሥ ኡምቤርቶና ከኢጣልያ መንግሥት ጋር በመደራደር የውጫሌው ውል እንዲጸድቅ መደረጉ ብቻ ሳይሆን ከኢጣልያኖቹ በተገኘው ብድር ብዙ የጦር መሣሪያዎች ለኢትዮጵያ ያስገኙ መሆኑ ነው። ተፈሪ መኰንን (በኋላ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ) የተወለዱትና እድሜያቸው ሶስት ዓመት እስኪሆን ድረስ የነበሩት በአባ ናዳ የበላይ ጠባቂነትና አሳዳጊነት በጃርሶ ጎሮ ነበር።

ስለኢትዮጵያ በዓለም ዙሪያ በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተሰሩ የከፍተኛ ትምሕርት መመረቂያ ጽሑፎች ጥንቅር Dissertations worldwide on Ethiopia in the English Language

ሰምና ወርቅ የጥናትና የምርምር መጽሔት ዝግጀት ክፍል ተቋርጦ የነበረውን ጠቃሚ የጥናት ሰነዶችን እና የምርምር ውጤቶችን ለአንባቢያን የማቅረቢያ ዓምዱን እንደገና ለመቀጠል ወስኗል::
በዚህ ዓምድ ለጊዜው የተገኙትን 170 ያገር ውስጥና የውጭ ሃገር ዩኒቨርሲቲዎች የከፍተኛ ዲግሪ ተመራቂዎች ለምረቃ ያቀረቧቸውን ሃገር-ተኰር የሆኑትን የጥናትና ምርምር ርእሶች ዝርዝር አቅርበናል::

የአስማት ጸሎት (ሳዶር አላዶር) ጌታቸው ኃይሌ ኒው ዮርክ ከተማ፤ ዩናይትድ ስቴትስ ሚያዝያ 15 ቀን 2011 ዓ.ም

በባህል ሲወርድ ሲዋረድ እንደደረሰን፥ አይሁድ ክርስቶስን ሲሰቅሉት በአምስት ምስማሮች (ችንካሮች) ቸንክረውት ነበር። እነዚህ ምስማሮች (ችንካሮች) በግሪክኛ ስም አላቸው፤ (1) ሳዶር፥ (2) አላዶር፣ (3) ዳናት፥ (4) አዴራ፥ (5) ሮዳስ ይባላሉ። እነሱንም የችንካሮቹ ስሞች እንደሆኑ ከማቆየት አልፈው፥ የአምላክ የምስጢር ስሞች ከሚሏቸው አስማት ጋራ ደባልቀው፥ ለመፍትሔ ሥራይ (መርዝና ድግምት ማርከሻ መዳኒት) የጸሎት ክፍል አደረጓቸው።

የኢትዮጵያ ጊዜያዊ ሁኔታና የመንፈሳዊ ፖለቲካ ራዕይ ከፈንታሁን ጥሩነህ (ዋሺንግተን ዲ.ሲ)

ሰኔ ወር 2010 ዓ.ም ጀምሮ በኢትዮጵያ ምድር የሚካሄደው የለውጥ ነፋስ አዲስና አስገራሚ ነው። በእግዚአብሔር ማመን ተስፋ አስቆርጧቸው የነበሩ ሁሉ ተገርመው የዶክተር አቢይ አህመድ አሊ በፖለቲካው መስክ መነሳት ላይ “የእግዚአብሔር እጅ አለበት” እስኪሉ ድረስ ሁኔታው ማራኪ ሆኖ ይገኛል። በምዕራቡና በምሥራቁ ዓለም የፖለቲካ ንድፈ-ሃሳቦችና ጽንሰ-ሃሳቦች የተራቀቁ ኢትዮጵያውያን ምሁራን በሁኔታው በመደመም የሚሉት አጥተው ዝምታን የመረጡበት ጊዜ ነው። አንዳንድ ዜጎች ደግሞ ይህ ክስተት ጊዜያዊ ቅዠት እንጂ እውን አይደለም በማለት ያላቸውን ግራሞት ይገልጻሉ። እኔ በበኩሌ በዶክተር አህመድ አሊ የሚመራው አዲሱ ፖለቲካ ሲጠበቅ የነበረው የእግዚአብሔር ጣልቃ ገብነት ያስከተለው መሆኑን አምናለሁ። ይህ እምነቴ ደግሞ ይህን መጣጥፍ እንድጽፍ ምክንያት ሆኖኛል።

ዘረመላዊ ሀብቶች አቅርቦትና ጥቅም ተካፋይነት (ገብርኤል ዳንኤል)

በከፍተኛ ብዝሀ ሕያወት (biological diversity) ፀጋ የታደለች አገር ናት። ብዝሀ ሕይወት በጣም ሰፊና የተወሳሰበ ዓለም አቀፋዊ ቀልብ የሳበ ከፍተኛ የሀብት፥ ምግብ ዋስትናና ንግድ ተፅእኖ ፈጣሪ ጉዳይ ነው። በኢትዮጵያ ከስድስት ሽህ በላይ የአዝርዕት ዝርያ እንዳሉ ይታወቃል። በባለቤትነት ወይም በብሔረ ሙላድነት (origin) የምትታወቅባቸው የብዝሀ ሕይወት ዝርያዎች በርካታ ናቸው። በኢትዮጵያ እነዚህ የተፈጥሮ ሀብቶች በተለያዩ መንገዶች ለሀገር ፍጆታም ሆነ ለውጭ ንግድ ጥቅም ላይ እንደሚውሉ ይታወቃል። በአዃያው የነዚህ የተፈጥሮ ሀብቶች ጥበቃ፥ እንክብካቤና ለንግድ በሚውሉበት ወቅት የማኅበረሰቡ ተሳትፎና ተጠቃሚነት በሚገባው መጠን እንዳልሆነ ይገመታል።

ያላዩት አገር ሲናፍቅ፥ የአዲስ መንግሥት ምኞት (ጌታቸው ኃይሌ)

“መቆየት መልካም ነው፤ የቆየ ሰው የማይሆን ነገር ሲሆን ያያል” ይባላል። ከማይሆኑ ነገሮች አንዱ ያላዩት አገር መናፈቅ ነው። ስለዚህ፥ “ያላዩት አገር አይናፍቅም” ይባላል። መቆየት መልካም ነው፥ እኔም ያላየሁት አገር እስኪናፍቀኝ ቆይቻለሁ። ግን የናፈቀኝ አዲስ ነገር ቢሆንም በኔ አልተጀመረም፤ መንፈሳውያን አባቶቻችንም ናፍቀውታል።

ፕሮፌሰር (አብርሃም) አቢይ ፎርድ

ፕሮፌሰር አቢይ ፎርድ በአዲስ አበባ ከተማ በ 1935 ዓ.ፈ. ተወለደ። አባቱና እናቱ ከባርቤዶስ ደሴት ወደ ኢትዮጵያ በመጡበት ጊዜ እናቱ ሚኞን ኢኒስ ፎርድ ባቋቋሙት የልዕልት ዘነበወርቅ ትምህርት ቤት የመማር እድል አግኝቷል። ወደ ዩናይትድ ስቴትስ በመምጣት ባገሩ አየር ኃይል ሰልጥኖ የጦር ጀቶችን ያበር ነበር። ኋላም በኮሎምቢያ ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነት ትምህርት ቤት ተመርቋል። ዋሺንግተን ዲ.ሲ በሚገኘው ሃዋርድ ዩኒቨርሲቲ እስከ…