የዐፄ ካሌብ ወይም የቅዱስ ኤልስባን* ገድል
ዐፄ ኢዛና ሃሌን ንጉሠ ነገሥት
ዘኢትዮጵያ ተብሎ አስር ዓመት
ከገዛ በኋላ ከልጆቹ መሃል የአክሱም
መኳንንት ካሌብን አነገሡ፤
ስመ ንግሡም ዳግማዊ
ዓፄ እለ አጽብሃ ንጉሠ ነገሥት
ዘኢትዮጵያ መሲሃ እግዚአብሔር
ተብሎ በ483 ዓም ነገሠ።
ሰላሳ አምስት ዘመን ከገዛ በኋላ
ሃይማኖቱ ኦሪታዊ የሆነ ዱኖባስ
ፊንሐስ በናግራን [አሁን የመን
ተብሎ በሚታወቀው]
የክርስቲያኖች ቁጥር መብዛቱን
አይቶ በግዛቱ ውስጥ የነበሩትን
ከአራት ሺ በላይ ክርስቲያኖችን
የገደለውን ንጉስ በማስወገዱ
ይታወቃል።