ዘረመላዊ ሀብቶች አቅርቦትና ጥቅም ተካፋይነት (ገብርኤል ዳንኤል)

በከፍተኛ ብዝሀ ሕያወት (biological diversity) ፀጋ የታደለች አገር ናት። ብዝሀ ሕይወት በጣም ሰፊና የተወሳሰበ ዓለም አቀፋዊ ቀልብ የሳበ ከፍተኛ የሀብት፥ ምግብ ዋስትናና ንግድ ተፅእኖ ፈጣሪ ጉዳይ ነው። በኢትዮጵያ ከስድስት ሽህ በላይ የአዝርዕት ዝርያ እንዳሉ ይታወቃል። በባለቤትነት ወይም በብሔረ ሙላድነት (origin) የምትታወቅባቸው የብዝሀ ሕይወት ዝርያዎች በርካታ ናቸው። በኢትዮጵያ እነዚህ የተፈጥሮ ሀብቶች በተለያዩ መንገዶች ለሀገር ፍጆታም ሆነ ለውጭ ንግድ ጥቅም ላይ እንደሚውሉ ይታወቃል። በአዃያው የነዚህ የተፈጥሮ ሀብቶች ጥበቃ፥ እንክብካቤና ለንግድ በሚውሉበት ወቅት የማኅበረሰቡ ተሳትፎና ተጠቃሚነት በሚገባው መጠን እንዳልሆነ ይገመታል።