እንሰት – ከቆጮና ቡላ ባሻገር
ይህ ጽሁፍ የእንሰትን ዘርፈብዙ ጠቀሜታና ታሪክ በተለይም መድኃኒትነቱ ላይ ያተኮረ ይሆናል። እንሰት፤ በሳይንሳዊ ስሙ እንሰት ቬንትሪኮሰም (Enset ventricosum or edule) ከዓለም ሁሉ በኢትዮጵያ ብቻ በምግብነት ጥቅም ላይ የዋለ ዘረ ሙላዱም ከኢትዮጵያ የሆነ የተክል ዓይነት ነው። የአገሪቷ አንድ አምስተኛ (20%) የሚሆነው ሃያ ስድስት ሚሊዮን (26 ሚሊዮን) ሕዝብ የእንሰት ተጠቃሚ እንደሆነ ይገመታል። ተክሉና ዝርያው ከሙዝ ጋር ተመሳሳይ ስለሆነ በእንግሊዝኛ “የውሽት ሙዝ” (false banana) ተብሎ ይታወቃል። እንሰት ከሶስት መቶ በላይ የተለያዩ ዝርያዎች አሉት። ግንዱ፤ ስሩ፤ ቅጠሉ (ኮባው) እና ቃጫው በብዛት ጥቅም ላይ ይውላሉ። እንሰት ከአስር ሺህ ዓመታት በላይ በኢትዮጵያ ሰሜን፥ ደቡብና ምዕራብ የታወቀና ጥቅም ላይ የዋለ እንደሆነ ታሪክ ይናገራል። በጣና ሐይቅ፣ በሰሜን ተራሮች ዙሪያ እንዲሁም እስከ ሰሜን አዲግራትና በደቡብ ኤርትራ በማእከላዊና ሰሜን ደጋማ አካባቢዎችም ያድግ እንደነበር ታሪክ ያስታውሳል። እንሰት ከሶስት መቶ በላይ የተለያዩ ዝርያዎች አሉት። እንደ ዝርያዎቹ ዓይነት ጠቀሜታዎቻቸውም እንዲሁ ይለያያሉ፤ ለምሳሌም ድርቅንና በሽታን ለመከላከል፤ ለመድኃኒነት፤ ለምግብነት፤ ለቤት መገልገያ፤ ለኢንዱስትሪ ግብአትነት ወዘተ። እንሰት በጉራጌ እሴት/እሰት፥ በሲዳሞ ዊሴ፥ በዳውሮና ወላይታ ኡጦ፥ በጌዴዎ ዎርኪቻ፥ በሃዲያ ስልጤና ከምባታ ዊሳ፥ በትግሬ ጉና ጉና በመባል ይታወቃል። ለብዙ የቤት አገልግሎት የሚውለው ቅጠሉ ኮባ ይባላል። በምግብነት የሚቀርበው ደግሞ እንደ አካባቢው ቆጮ (ዉሳ፥ ዋሳ፥ ወርቄ…)፥ አሚቾ፥ቡላ ወዘተ እየተባለ ይጠራል።
የእንሰትን ጠቃሚነት እንደሌሎች አዝእርቶች እውቅና መስጠት፤ የወደፊቱ አንዱ የግብርና ምሰሶ ማድረግ፤ በዋጋ ዝቅተኝነትና አትራፊ የሆኑ ምርቶች ላይ በማትኮር የእንሰት ግብርና እንዳይመነምን የእንሰት አምራቾች እንዲበረታቱ ማድረግ ይገባል።
(ሙሉ ጽሑፉን ለማንበብ ዓርእስቱን ይጫኑ)



















