የሕይወት ታሪክ

የሕይወት ታሪክ, ጥናትና ምርምር, ፖለቲካ

የታኅሳስ 1953 ዓ.ም ግርግር በከፊል – ከሻለቃ ያሬድ ቢተው – ዋሺንግተን ዲሲ፣ ሰሜን አሜሪካ – ጥቅምት 2017 ዓ.ም

በጽሁፉ ውስጥ የተካተቱት ቁምነገሮች የመጀመሪያ ደረጃ ምልከታ ምዝገባ ተብለው ከሚጠቀሱት የታሪክ ማጣቀሻ ማስረጃዎች ውስጥ የሚካተቱ ናቸው።
በስነ-ጽሁፍ አቀራረብ ረገድ በወቅቱ የነበረውን የጦማር አጻጻፍ ስልት አጉልቶ በማሳየት በዘመናት መካከል የተፈጠረውን የደብዳቤ እንዲሁም ታሪክ አዘጋገብ የእድገት ወይም ውድቀት ደረጃ አጉልቶ የሚያሳይ በመሆኑ ለስነጽሁፍ ተመራማሪዎች የሚሰጠው ፋይዳ ቀላል አይሆንም።
ከታሪክ አንጻር የወሰድነው እንደሆነ በወቅቱ የተሟላ ማስረጃ ያልተገኘላቸውን እውነታዎች ለህብረተሰባችንና ለታሪክ ተመራማሪዎች በመስጠቱ ረገድ የላቀ አስተዋጻኦ ይኖረዋል:: በዋናነትም የግለታሪክ ዘጋቢው በኩነቱ ወቅት እርምጃው በተወሰደባቸው ቀናት ውስጥ ተሳታፊ የነበሩ በመሆናቸው በአይናቸው የተመለከቱትን የዘገቡ በመሆኑ ከዚህ በፊት ኩነቱን አስመልክቶ የተጻፉ የጥናትና ምርምር ስራዎች ጉድለት በማሟላቱ ረገድ ፋይዳው የጎላ ነው።
የሰምና ወርቅ መጽሔት አዘጋጅዎች

ታሪክ, የሕይወት ታሪክ, ጥናትና ምርምር

የሻምበል ሲስተር አስቴር አያና አጭር የሕይወት ታሪክ ከልጃቸው ከያፌት አስራት – ነሐሴ ፲፪, ፳፻፲፭ (August 18, 2023)

የተባበሩት መንግስታት ዋና ጸሐፊ ዳግ ሃመርሾልድ ለግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ የላኩት ቴሌግራም:- “ስሟን ገና ያላወቅነው አንዲት ኢትዮጵያዊት ነርስ አንድ አሜሪካዊ መኮንን በአንድ ጂፕ መኪና ውስጥ ተይዞ ሲደበደብ ብቻዋንና ባዶ እጅዋን ልታድነው በሙሉ ልበኝነት ሞክራ ሳይሆንላት ቢቀር ኮንጎዎቹ አሜሪካኑን ይዘዉት ሲሄዱ ሰፈራቸው ድርስ ተከትላ ሔደች፡፡ እዚያም በጥይት ሊገድሏት ቢያስፈራሯትም ተመልሳ ወሬውን ለኢትዮጵያውያኑ ነግራ ሶስቱን አሜሪካውያን አድነዋቸዋል፡፡”  ንጉሡ በመልሳችው ለሲስተር የላኩት መልእክት ” ሥራሽ  ላይ ሆነሽ በፈጸምሸው መልካም ተግባር በጣም ተደስተናል፡፡ ስለ መልካም ሥራሽና ስለ መልካም አደራጎትሽ በጣም እናመሰግንሻለን” ብለው ነበር፡፡ ሲስተርም  በትህትና ሲመልሱ  “ላደርገው የሚገባኝን አገልግሎት በመፈጸሜ የግርማዊነትዎ የምስጋና ቴሌግራም ስለ ደረሰኝ ፤ አነስተኛ አገልጋይዎን በምስጋና ላሰበኝ ግርማዊነትዎ እድሜ በመለመን መሬት እስማለሁ” በማለት ነበር ፡፡

ሥነጽሑፍ, የሕይወት ታሪክ, ጥናትና ምርምር

የአቶ ሰይፉ መታፈሪያ የሥነግጥም መድብሎች የጥናት እና የምርምር ሥራዎች ።

ገጣሚ ሲቆጣ (ሰይፉ መታፈሪያ)፣
መጻፍ፣ መጻፍ አለኝ ማቅለም ወረቀት፣ ብእሬን ማስቆጣት ቀይ ደም ማስተፋት።

ዕውቁ ገጣሚ፣ መምህር እና የፎክሎር ባለሙያ ሰይፉ መታፈሪያ ፍሬው በርካታ ያገራችንን እና የአውሮጳን ቋንቋዎች አጥርተው የሚናገሩ እና ጠንቅቀው የሚያውቁ ልሳነ ብዙ ምሁርና ተመራማሪ ናቸው። በኢትዮጵያ እጅግ የተለየ የግጥም አጻጻፍ ስልትን ያስተዋወቁና ያስፋፉ ዕውቅ ገጣሚ ናቸው። እሳቸው እንደሚሉት የግጥማቸው የአጻጻፍ (ዓይነት) „በብዙ ረገድ ባህል-ከተል አይደለም። በዚህ ያጻጻፍ አዲስነት አስገዳጅነትም ስም ስላስፈለገው „ስንኝ አጠፍ ግጥም“ የሚል ስያሜ ሰጥተውታል። ላለፉት ሃምሳ ዓመታት በሀገራችን ቁጥራቸው በርካታ የሆኑ የፎክሎር እና የሥነ ጽሑፍ ተማሪዎችን እና ምሁራንን አፍርተዋል።

ዜና እረፍት, የሕይወት ታሪክ

ተዝካረ ሕይወት – አህመድ ኑር (1949 – 2014 ዓ.ም)

አቶ አህመድ ኑር፤ የሃገሩ ነገር የሚያንገበግበው ፣ የሚቆረቁረው፣ እምነቱንም የሚወድና የሰውን ልጅ ባጠቃላይ የሚያከብርና ጓደኞቹን የሚወድ፤ ባንፃሩ ደግሞ በሰው ዘንድ ተወዳጅ የነበረ ወንድማችን ነበር። በሚጽፋቸው ግጥሞቹ ግጥም የመግጠም ልዩ ችሎታ እንደነበረው ገላጭ ናቸው። በየስብሰባዎች ላይ የሚያነሳቸው ጥያቄዎቹ ሁሉ ጥበብን የተሞሉና ማንንም የማይጎዱ ከአሽሙርና ከአግቦ አገላለጾች ነፃ የሆኑ ቀጥተኛ ነበሩ። ከወሎ ማደጉን እንደትልቅ ነገር የሚያወሳው አቶ አህመድ ኑር የወሎን ዙሪያ ባህልና የንግግር ዘዬ አሳምሮ መግለጽ በመቻሉ የወሎ አምባሳደር የሆነ ያህል ያስቆጥረው ነበር።

የሕይወት ታሪክ

`ዔርታ~ዓሌ`፡~በእንተ፡ነገረ፥`ድንቂቱ`

“`ዔርታ፡ዓሌ፥ወበእንተ፡ነገራ፡ለ`ድንቂቱ`ተረክ ጭብጡ ዕውን ላይ የተመሠረተ ታሪክ ነው” ጃህእርሥዎ፡ሞትባይኖር፡ኪሩብ፡ዔል`፡~ በሚል መጠሪያ ለመጀመሪያ ጊዜ የምናትምለትን ይህን “ዔርታዓሌ ወበእንተ ነገራ ለድንቂቱ” በሚል ርዕስ ባቀረበው ትርክት እንዲታወቅ ቢፈልግም፣ በተለምዶ ስሙ “ጃርሶ ኪሩቤል”ተብሎ የሚታወቀው ይኸው ደራሲና ፀሐፊ በኪነ~ጥበብ ሙያ እና በ( ዔዞቴሪክ~ሳይንስ)ኅቡዕ የነገረ-ሰብ ጥናት እና ምርምር ላይ የተሰማራ ሰው ነው።

የሕይወት ታሪክ

አቶ ዳምጤ አሰማኸኝ (አጭር የህይወት ታሪክ)

ከሁሉ አስቀድሜ የመጽሐፌን ርዕስ “የተዘጋው ምዕራፍ” ብዬ የሰየምኩበትን ምክንያት ልግለጽ። ምክንያቴ ቀላል ነው። ማንኛውም ሰው በራሱ እንጂ በአያትና በቅድመ አያቶች ጥፋት መቅቀጣት እንደሌለበት አምናለሁ። ያ፥ ለኔ የተዘጋ
ምዕራፍ ነውና። ይህን ታሪክ የጻፍኩበት የአባቶቻችንን ስህተት እንዳንደግም፥ ያለሙትን ደግሞ እንድናዳብር እንጂ “አያትህ አያቴን በድሎታልና ብድሩን በአንተ ላይ መመለስ አለብኝ” እየተባባልን እርስ በርሳችን ስንናቆር እንድንኖር አይደለም። ከዓለም ሕዝብ ሁሉ ወደሗላ ያስቀረን ይሄው ተከፍሎ የማያልቅ የበቀል ዕዳ ይመስለኛል። ለዚህ ነው ያ የበቀል ምዕራፍ እንዲዘጋ የፈለግሁት ምጽሐፉንም “የተዘጋው ምዕራፍ” ያልኩት።

ሥነጽሑፍ, ታሪክ, የሕይወት ታሪክ

መሪራስ አማን በላይ (፲፱፻፵፪-፳፻፱)

በ1997 ዓ.ም ገደማ ከአማን በላይ መተዋወቅ እንደጀመርን በየጊዜው እየተደዋወልን ለረጅም ሰዓቶች በስልክ እናወራ ነበር። ለሀገሩ ሰው ያለውን ሁሉ ዕውቀት የማካፈል ምኞት ስለነበረው አብዛኛውን ጊዜ የሚናገረው እርሱ ነው። እጅግ ሰፊ ትንታኔና ሐተታ ማቅረብ ይችል ነበር።

Scroll to Top