ሥነጽሑፍ

ሥነጽሑፍ, ቁጥር 2

“ኪነጥበብ እና ሥነጥበብ” (ይትባረክ ገሠሠ)

“ይህ ጽሑፍ መሠረታዊ ብለን ከምንመድባቸው ጽሑፎች ይመደባል። በተለምዶ የሚሠራባቸውን ቃላት ከትክክለኛው መሠረታቸው (መነሻቸው) ጋር አያይዞ ትክክለኛውን ፍችና ጥቅም እንዲሰጡ ሙከራ ያደርጋል። በተለይም የግዕዝ ቋንቋ ያለውን ጥቅም ለማወቅ ይረዳል ብለን እንገምታለን።”

ሥነጽሑፍ, ቁጥር 2

“ቅኔና ፅንሰ ሀሳቦቹ – ክፍል 1” (ፈንታሁን ጥሩነህ)

“ይህ ጽሑፍ የቅኔ ቤት ወይም የቅኔ ትምህርት ቤት ተብሎ የሚታወቀውን ጥንታዊ ተቋም ይመለከታል። ጥናቱም ቅኔና የሥነጽሑፍ ተግባሩን፣ ቅኔና የንድፈ ሀሳብ አወቃቀሩን፣ እና ቅኔና የፍልስፍና ተግባሩን ይዳስሳል።”

ሥነጽሑፍ, ቁጥር 1, ባህል

ባህል ሥነጽሑፍና ኪነጥበብ

በኢትዮጵያ ከየብሔረሰቡ የሚፈልቁ ብዙ አሸብራቂና አስደሳች ትርጉም የሚሰጡ የባሕል ቅርሶች አሉ ። ብዙ ዓይነት ጣዕመ ዜማ ያላቸው የሙዚቃ መሳሪያዎችም ቁጥራቸው በርካታ ነው። ብሔራት የባህላቸውን ምንነት የሚገልጹባቸው የራሳቸው የሆነ የስእልና የቅርጻ ቅርጽ አቀራረጽ አሳሳልና ልዩ ልዩ ብልሃት ሞልቷል። ይህ ሁሉ አስደናቂ ነገር አብይ ቅርስ ስለሆነ ይህ ትውልድ የራሱ የሆነውን ቅርሳዊ ሃብት ኮርቶበት ለመጪው ትውልድ በቂ መሰረት ለማቆየት አካባቢውን አጥንቶና መርምሮ ማወቅና ማሳወቅ ማቆየት ይገባዋል።

Scroll to Top