Uncategorized

ሳይንስ, ባህል, ታሪክ, Uncategorized

እንሰት – ከቆጮና ቡላ ባሻገር

ይህ ጽሁፍ የእንሰትን ዘርፈብዙ ጠቀሜታና ታሪክ በተለይም መድኃኒትነቱ ላይ  ያተኮረ ይሆናል። እንሰት፤ በሳይንሳዊ ስሙ እንሰት ቬንትሪኮሰም (Enset ventricosum or edule) ከዓለም ሁሉ በኢትዮጵያ ብቻ በምግብነት ጥቅም ላይ የዋለ ዘረ ሙላዱም ከኢትዮጵያ የሆነ የተክል ዓይነት ነው። የአገሪቷ አንድ አምስተኛ (20%) የሚሆነው ሃያ ስድስት ሚሊዮን (26 ሚሊዮን) ሕዝብ የእንሰት ተጠቃሚ እንደሆነ ይገመታል። ተክሉና ዝርያው ከሙዝ ጋር ተመሳሳይ ስለሆነ በእንግሊዝኛ “የውሽት ሙዝ” (false banana) ተብሎ ይታወቃል። እንሰት ከሶስት መቶ በላይ የተለያዩ ዝርያዎች አሉት። ግንዱ፤ ስሩ፤ ቅጠሉ (ኮባው) እና ቃጫው በብዛት ጥቅም ላይ ይውላሉ። እንሰት ከአስር ሺህ ዓመታት በላይ በኢትዮጵያ ሰሜን፥ ደቡብና ምዕራብ የታወቀና ጥቅም ላይ የዋለ እንደሆነ ታሪክ ይናገራል።  በጣና ሐይቅ፣ በሰሜን ተራሮች ዙሪያ እንዲሁም እስከ ሰሜን አዲግራትና በደቡብ ኤርትራ በማእከላዊና ሰሜን ደጋማ አካባቢዎችም ያድግ እንደነበር ታሪክ ያስታውሳል። እንሰት ከሶስት መቶ በላይ የተለያዩ ዝርያዎች አሉት። እንደ ዝርያዎቹ ዓይነት ጠቀሜታዎቻቸውም እንዲሁ ይለያያሉ፤ ለምሳሌም ድርቅንና በሽታን ለመከላከል፤ ለመድኃኒነት፤ ለምግብነት፤ ለቤት መገልገያ፤ ለኢንዱስትሪ ግብአትነት ወዘተ። እንሰት በጉራጌ እሴት/እሰት፥ በሲዳሞ ዊሴ፥ በዳውሮና ወላይታ ኡጦ፥ በጌዴዎ ዎርኪቻ፥ በሃዲያ ስልጤና ከምባታ ዊሳ፥ በትግሬ ጉና ጉና በመባል ይታወቃል። ለብዙ የቤት አገልግሎት የሚውለው ቅጠሉ ኮባ ይባላል።  በምግብነት የሚቀርበው ደግሞ እንደ አካባቢው ቆጮ (ዉሳ፥ ዋሳ፥ ወርቄ…)፥ አሚቾ፥ቡላ ወዘተ እየተባለ ይጠራል።
የእንሰትን ጠቃሚነት እንደሌሎች አዝእርቶች  እውቅና መስጠት፤ የወደፊቱ አንዱ የግብርና ምሰሶ ማድረግ፤ በዋጋ ዝቅተኝነትና አትራፊ የሆኑ ምርቶች ላይ በማትኮር የእንሰት ግብርና እንዳይመነምን የእንሰት አምራቾች እንዲበረታቱ ማድረግ ይገባል።
(ሙሉ ጽሑፉን ለማንበብ ዓርእስቱን ይጫኑ)

ሀይማኖት, ሥነጽሑፍ, Uncategorized

ስለኢትዮጵያ፡ደራሲያን።

ጽሑፉ፡የፕሮፌሰር፡ታምራት፡አማኑኤል፡ነው። ፕሮፌሰር፡ታምራት፡ከሰማንያ፡ዓመታት፡በፊት፡በትምርትና፡ሥነጥበብ፡ሚኒስቴር፡አማካሪ፡ኾነው ይሠሩ፡ነበር። ነገር፡ግን፡በዚያን፡ጊዜ፡ፕሮፌሰር፡በመባል፡ፈንታ፡ሊቀማእምራን፡ይባሉ፡ነበር። ፕሮፌሰሩ ሲናገሩም :- “ባ፩ኛው፡ዘመን፡በዐማርኛ፡የተጻፈው፡ሥራ፡ እጅግ፡ጥቂት፡ነው።የተጻፈውም፡ላንዳንድ፡ነገሥታት ምስጋና፡ደራሲው፡ካልታወቀ፡የተገጠመ፡ቅኔ፡ነው። ቅኔውም፡በዘመናት፡ውስጥ፡አንድ፡ቋንቋ፡እንደምን፡ ኹኖ፡እየተለዋወጠ፡ለመኼዱ፡ዋና፡ምስክር፡ከመኾኑ በላይ፣በዚያ፡ዘመን፡የነገሥታቱ፡ሥልጣንና፡የተዘረጋበት፡የሰፊው፡አገር፡ኹኔታ፡እንዴት፡እንደነበረ፣ለታ ሪክና፡ለዦግራፊም፡ማስረጃ፡ለመኾን፡ይረዳል። ዐማርኛው፡ዛሬ፡ዘመን፡የማንናገርበትና፡የማንጽፈው፣ለማስተዋሉም፡የሚያስቸግረንና፡የሰዋስው፡አካኼድ፡የተለዋወጠ፡ብዙ፡ቃልና፡አገባብ፡አለበት። እርሱን፡የመሰለ፡ዐማርኛም፡በየዘመኑ፡እየተጻፈ፡ምናልባት፡እስከ፡ ፲፭፻፺፱-፲፮፻፯፡ደርሶ፡ ይኾናል።”

Uncategorized

ቀኛዝማች አባ ናዳ፤ (ቀኛዝማች ድልነሣሁ ጠንፉ) የኢትዮጵያ ጀግናና ዲፕሎማት ከኪዳኔ ዓለማየሁ

አባ ናዳ ከቅርብ ዘመዳቸው ከልዑል ራስ መኰንን ወልደሚካኤል ጋር በመዝመት ሐረርጌ በቅኝ ገዥዎች እንዳትያዝ ካደረጉት ጀግኖች አንዱ ናቸው። ዓረቦች፣ እንግሊዞች ፣ ፈረንሳዮችና ኢጣልያኖች ሐረርጌን ለመያዝ አሰፍስፈው በነበረበት ጊዜ በአጼ ምኒልክ ብልሕና ፈጣን እርምጃና አመራር በነራስ መኰንንና አባ ናዳ ቆራጥነት ሐረርጌን ለማዳን ችለዋል። አባ ናዳ መኖሪያቸውን ጃርሶ ጎሮ አድርገው በልዑል ራስ መኰንን መሪነት ሐረርጌ ከሌላው የኢትዮጵያ ክፍለ-ግዛት ጋር የነበራት ትስስር እንዲጠናከር አድርገዋል። አባ ናዳን አስደናቂ የሚያደርጋቸው ሌላው ከፍ ያለ ቁምነገር በ1889 ዓ/ም ከራስ መኰንን ጋር ኢጣልያ ተጉዘው ከልዑካኑ ጋር በመሆን በጊዜው ከነበሩት ከንጉሥ ኡምቤርቶና ከኢጣልያ መንግሥት ጋር በመደራደር የውጫሌው ውል እንዲጸድቅ መደረጉ ብቻ ሳይሆን ከኢጣልያኖቹ በተገኘው ብድር ብዙ የጦር መሣሪያዎች ለኢትዮጵያ ያስገኙ መሆኑ ነው። ተፈሪ መኰንን (በኋላ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ) የተወለዱትና እድሜያቸው ሶስት ዓመት እስኪሆን ድረስ የነበሩት በአባ ናዳ የበላይ ጠባቂነትና አሳዳጊነት በጃርሶ ጎሮ ነበር።

Scroll to Top