“ፍትሐ ነገሥት እና የጥንቱ ፍርድ ሥርዐት” (ያዕቆብ ኃይለማርያም )
“ፍትሐ ነገሥትና በወቅቱ የነበረው የፍርድ አሰጣጥ የዘመኑ ማኅበረሰብ ሥርዐት ነጸብራቅ እንደመሆኑ መጠን የሰጠው ግልጋሎትም ማኅበረሰቡን በየደረጃው ከፋፍሎ ነው።”
“ፍትሐ ነገሥትና በወቅቱ የነበረው የፍርድ አሰጣጥ የዘመኑ ማኅበረሰብ ሥርዐት ነጸብራቅ እንደመሆኑ መጠን የሰጠው ግልጋሎትም ማኅበረሰቡን በየደረጃው ከፋፍሎ ነው።”
የምንነሳው ኢትዮጵያ በታሪኳ ጥንታዊነት መታወቋን ምርኩዝ በማድረግ ነው። ይህ ሲባል ግን ጥንታዊ ታሪኳ በጅምላ የሚያኮራ ነበር ከሚል ትምክት ለመነሳት አይደለም። ከዚህ ጥንታዊነት ጋር ተያይዞ ሲወርድ ሲዋረድ የመጣውን ባህልና ያሁኑ ትውልድ የወረሰውን ማንኛውንም ታሪክ መመልከት ይኖርብናል። የጥንትና የቅርቡ ታሪክ በሚነሳበት ጊዜ የምንማረው ምንድነው ከሚል ጥያቄ አንፃር መሆን ይኖርበታል። መጥፎውን መጥፎ፣ ጥሩውን ጥሩ ለማለት ግን ታሪክን የምናይበትና የምንመረምርበት መመልከቻ ዘዴ የግዴታ እንዲኖረን ሊያስፈልግ ነው።