የቀደሙት እትሞች
“የጨዋታ ትችት” [ግምገማ] (ዮናስ አድማሱ)
“መጽሐፉ ትእግሥትን ይጠይቃል፤ በገጽ ብዛት ዳጎስ በማለቱ አይደለም (“ፍቅር እስከ መቃብር” ይበልጣል፣ “አንድ ለናቱ” ይብሳል)። ለብዙዎቻችን አማርኛው እንግዳ ነው። የሚያስደነግጥ፣ ስለዚህም የሚያሸሽ የሚመሳስለው የዐረፍተ ነገሮቹ አሰካክና ባካባቢው ልዩ ዘየ ተታሸው የጨዋታ ዘይቤ ወይም ዚቅ ነው።”
“ረኀብና ተስቦ በኢትዮጵያ” (ጌታቸው ኃይሌ)
“ረኃብና ተስቦ በኢትዮጵያ በታሪክ በኩል የቱን ያህል እንደነበሩ ለማሳየት አንዳንድ ማስታወሻዎችን ከታሪክ ገጾች ልጥቀስ።”
“ረሃብ ድርቅና መንስኤዎቻቸው” (ገብርኤል ዳንኤል)
“ይህ ጽሑፍ ከሞላ ጐደል ረሃብና ድርቅ ሰው ሰራሽ ችግር ነው፤ ስለዚህም መፍትሔው ሰው ሰራሽ ነው ወደሚለው ያዘማል።”
“የኢትዮጵያ ረሀብና የምዕራብ ጋዜጦች” (እነ ቆሪቾ ፈይሣ)
“የምዕራቡ ጋዜጣ አዘጋጅዎችና ሪፖርተሮች ከአባቶቻቸው ኮሎኒያሊስቶች የተረከቡትን ኢትዮጵያን የማጥላላት ዘመቻ ዛሬ ኢትዮጵያ በደረሰባት አሳዛኝ ማኅበራዊ ቀውስ ሳቢያ በማስታከክ ነባር ቂማቸውንና አዲስ ርዕዮተ ዓለማዊ ጥላቻቸውን ለመወጣት በጽሑፎቻቸው ይቃጣቸዋል።”
“ሰላም በኤርትራ” (ያዕቆብ ኃይለማርያም)
“ከአሜሪካ ሆኖ ስለኤርትራ ችግር መወያየት በመሠረቱ የተሟላ ሊሆን ባይቻልም አንድ ሃሳብ ከየትም ይመንጭ ከየትም የሚቀርበው ሃሳብና ትችት ቀጥተኛና የተባ ውጤት ሊኖረው ይችላል።”
“የብላቴን ጌታ ማኅተመ ሥላሴ ወልደ መስቀል የሕይወት ታሪክ”
“ከዚህ ቀጥሎ የታተመው ራሳቸው ያረቀቁት የሕይወት ታሪካቸው የተገኘው ከቤተሰቦቻቸው ሲሆን የሕይወት አመራራቸውን በቅርብ ሆነው የተከታተሉ ቤተሰቦቻቸው የጻፉት መግቢያ ጽሑፍ አብሮ ቀርቧል።”
“ኢትዮጵያ” የሚለው ቃል
“ኢትዮጵያ የሚለው ቃል ምን ማለት ነው? ከወዴትስ የመጣ ቃል ነው? የሚሰጡት መልሶች ግን አጥጋቢ አይደሉም። እንዲያውም አልፎ አልፎ ጥራዝ ነጠቅና የተዛባ የተሳሳተም መልስ ሲሰጥ እንሰማለን።”







