ስለኢትዮጵያ፡ደራሲያን።

ባ፩ኛው፡ዘመን፡በዐማርኛ፡የተጻፈው፡ሥራ፡ እጅግ፡ጥቂት፡ነው።የተጻፈውም፡ላንዳንድ፡ነገሥታት ምስጋና፡ደራሲው፡ካልታወቀ፡የተገጠመ፡ቅኔ፡ነው። ቅኔውም፡በዘመናት፡ውስጥ፡አንድ፡ቋንቋ፡እንደምን፡ ኹኖ፡እየተለዋወጠ፡ለመኼዱ፡ዋና፡ምስክር፡ከመኾኑ በላይ፣በዚያ፡ዘመን፡የነገሥታቱ፡ሥልጣንና፡የተዘረጋበት፡የሰፊው፡አገር፡ኹኔታ፡እንዴት፡እንደነበረ፣ለታ ሪክና፡ለዦግራፊም፡ማስረጃ፡ለመኾን፡ይረዳል። ዐማርኛው፡ዛሬ፡ዘመን፡የማንናገርበትና፡የማንጽፈው፣ለማስተዋሉም፡የሚያስቸግረንና፡የሰዋስው፡አካኼድ፡የተለዋወጠ፡ብዙ፡ቃልና፡አገባብ፡አለበት። እርሱን፡የመሰለ፡ዐማርኛም፡በየዘመኑ፡እየተጻፈ፡ምናልባት፡እስከ፡ ፲፭፻፺፱-፲፮፻፯፡ደርሶ፡ ይኾናል።

የዐፄ ካሌብ ወይም የቅዱስ ኤልስባን* ገድል

ዐፄ  ኢዛና  ሃሌን ንጉሠ ነገሥት 
ዘኢትዮጵያ ተብሎ አስር ዓመት 
ከገዛ በኋላ ከልጆቹ መሃል የአክሱም 
መኳንንት ካሌብን አነገሡ፤ 
ስመ ንግሡም ዳግማዊ 
ዓፄ እለ አጽብሃ ንጉሠ ነገሥት 
ዘኢትዮጵያ መሲሃ እግዚአብሔር 
ተብሎ በ483 ዓም ነገሠ።
ሰላሳ አምስት ዘመን ከገዛ በኋላ 
ሃይማኖቱ ኦሪታዊ የሆነ ዱኖባስ 
ፊንሐስ በናግራን [አሁን የመን 
ተብሎ በሚታወቀው] 
የክርስቲያኖች ቁጥር መብዛቱን 
አይቶ በግዛቱ ውስጥ የነበሩትን 
ከአራት ሺ በላይ ክርስቲያኖችን  
የገደለውን ንጉስ በማስወገዱ 
ይታወቃል። 

የኢትዮጵያውያን ገዳምና ተማሪ-ቤት በቫቲካን፤ ግርማይ ተስፋጊዮርጊስ፤ ሰሜን አሜሪካ (ጥር 2012 ዓም)

ኢትዮጵያውያን ነጋድያን (ፕልግርምስ) ከአስራ አምስተኛ ክፍለዘመን ጀምረው የቅዱስ ጴጥሮስና የቅዱስ ጳውሎስ መቃብር ለመሳለም ወደ ሮም ይሄዱ እንድነበረ በቫቲካን መዛግብትና በኣንዳኣንድ የታሪክ ጸሓፊዎች ሰነዶች ተጽፎ ይገኛል። የሮም ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ለነዚህ ነጋድያን በቫቲካን ውስጥ የሚገኝ የትልቁ ቅዱስ ኢስጢፋኖስ ገዳም የሚባል ጥንታዊ ቤተክርስቲያን ከነ እንግዳ መኖርያ ቤት ሰጡዋቸው። ይህ ቤተክርስቲያን ለኢትዮጵያውያን ከተበረከተ በኋላ Santo Stefano Dei Mori “የቀይ ዳማዎች ቅዱስ ኢስጢፋኖስ” ተባለ። ከዛን ጊዜ ጀምሮ ይህ ቦታና ገዳም በኢየሩሳሌም በኩል ወደ ሮም ይሄዱ የነበሩ ኢትዮጵያውያን መነኮሳት ንብረት ሆኑ። መነኵሴዎቹ ከየትኞች የኢትዮጵያ ገዳሞች ይመጡ እንደነበረ ሁሉ በቫቲካን መዛግብት ተጽፎ ይገኛል። ደብረ-ዳሞ፣ ደብረ-ሊባኖስ፣ ደብረ-ቢዘን ወዘተ ለምሳሌ ሊጠቀሱ ይችላሉ፡፡ ይህ ከፍ ያለ ክብርና ታሪክ ያላት ብቸኛ ኣንዲት ኮሌጅ በቫቲካን ውስጥ መኖር ለኢትዮጵያ ህዝብ ትልቅ ክብር ነው። ስለዚህም የኢትዮጵያ ታልላቅ ሰዎችና ባለስልጣናት ወደ አውሮጳ ሲሄዱ ይህችን ኮሌጅ ሳይጎበኙ አያልፉም ነበር። ለምሳሌ ቀዳማዊ ኃይለስላሴ ሁለት ጊዜ፣ (አልጋውራሽ እያሉ በ1924 እና ንጉሠ-ነገሥት እያሉ በ1970 ዓ ም) ፥ ልዕልት ተናኘ ወርቅና ልዑል አስፍሓ ወሰን በ1932 ዓ. ም. በቅርቡም ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በ2019 ወዘተ. ይገኙበታል።

የአስማት ጸሎት (ሳዶር አላዶር) ጌታቸው ኃይሌ ኒው ዮርክ ከተማ፤ ዩናይትድ ስቴትስ ሚያዝያ 15 ቀን 2011 ዓ.ም

በባህል ሲወርድ ሲዋረድ እንደደረሰን፥ አይሁድ ክርስቶስን ሲሰቅሉት በአምስት ምስማሮች (ችንካሮች) ቸንክረውት ነበር። እነዚህ ምስማሮች (ችንካሮች) በግሪክኛ ስም አላቸው፤ (1) ሳዶር፥ (2) አላዶር፣ (3) ዳናት፥ (4) አዴራ፥ (5) ሮዳስ ይባላሉ። እነሱንም የችንካሮቹ ስሞች እንደሆኑ ከማቆየት አልፈው፥ የአምላክ የምስጢር ስሞች ከሚሏቸው አስማት ጋራ ደባልቀው፥ ለመፍትሔ ሥራይ (መርዝና ድግምት ማርከሻ መዳኒት) የጸሎት ክፍል አደረጓቸው።