“የጨዋታ ትችት” [ግምገማ] (ዮናስ አድማሱ)

“መጽሐፉ ትእግሥትን ይጠይቃል፤ በገጽ ብዛት ዳጎስ በማለቱ አይደለም (“ፍቅር እስከ መቃብር” ይበልጣል፣ “አንድ ለናቱ” ይብሳል)። ለብዙዎቻችን አማርኛው እንግዳ ነው። የሚያስደነግጥ፣ ስለዚህም የሚያሸሽ የሚመሳስለው የዐረፍተ ነገሮቹ አሰካክና ባካባቢው ልዩ ዘየ ተታሸው የጨዋታ ዘይቤ ወይም ዚቅ ነው።”

“የኢትዮጵያ ረሀብና የምዕራብ ጋዜጦች” (እነ ቆሪቾ ፈይሣ)

“የምዕራቡ ጋዜጣ አዘጋጅዎችና ሪፖርተሮች ከአባቶቻቸው ኮሎኒያሊስቶች የተረከቡትን ኢትዮጵያን የማጥላላት ዘመቻ ዛሬ ኢትዮጵያ በደረሰባት አሳዛኝ ማኅበራዊ ቀውስ ሳቢያ በማስታከክ ነባር ቂማቸውንና አዲስ ርዕዮተ ዓለማዊ ጥላቻቸውን ለመወጣት በጽሑፎቻቸው ይቃጣቸዋል።”

“ኢትዮጵያ” የሚለው ቃል

“ኢትዮጵያ የሚለው ቃል ምን ማለት ነው? ከወዴትስ የመጣ ቃል ነው? የሚሰጡት መልሶች ግን አጥጋቢ አይደሉም። እንዲያውም አልፎ አልፎ ጥራዝ ነጠቅና የተዛባ የተሳሳተም መልስ ሲሰጥ እንሰማለን።”