ዘረመላዊ ሀብቶች አቅርቦትና ጥቅም ተካፋይነት (ገብርኤል ዳንኤል)

በከፍተኛ ብዝሀ ሕያወት (biological diversity) ፀጋ የታደለች አገር ናት። ብዝሀ ሕይወት በጣም ሰፊና የተወሳሰበ ዓለም አቀፋዊ ቀልብ የሳበ ከፍተኛ የሀብት፥ ምግብ ዋስትናና ንግድ ተፅእኖ ፈጣሪ ጉዳይ ነው። በኢትዮጵያ ከስድስት ሽህ በላይ የአዝርዕት ዝርያ እንዳሉ ይታወቃል። በባለቤትነት ወይም በብሔረ ሙላድነት (origin) የምትታወቅባቸው የብዝሀ ሕይወት ዝርያዎች በርካታ ናቸው። በኢትዮጵያ እነዚህ የተፈጥሮ ሀብቶች በተለያዩ መንገዶች ለሀገር ፍጆታም ሆነ ለውጭ ንግድ ጥቅም ላይ እንደሚውሉ ይታወቃል። በአዃያው የነዚህ የተፈጥሮ ሀብቶች ጥበቃ፥ እንክብካቤና ለንግድ በሚውሉበት ወቅት የማኅበረሰቡ ተሳትፎና ተጠቃሚነት በሚገባው መጠን እንዳልሆነ ይገመታል።

“የኢትዮጵያውያን የሳይንስ ሙያተኞች ድርጅት” (ሰይፉ በላይ)

“የዚህ ድርጅት ዋና ዓላማ በሳይንስና ቴክኖሎጂ ጥናትና ምርምር የሚያካሂድና የሚያቀናጅ ስለሚሆን በተለይም ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ የሳይንስ ምሁራን በውጭ ከሚገኘው ኢትዮጵያዊ የሳይንስ ሙያተኛ ጋር ተገናኝተው የጥናትና ምርምር ተለምዶ የሚለዋወጡበትና የሚረዳዱበትን መንገድ የሚፈልጉበት መንኮራኩር መሆን ነው።”

“የወባ በሽታን ስለማጥፋት የተደረገ ልማዳዊ ጥናት” (ዮሐንስ)

“ለወባ በሽታ ያገኘሁት የባህል መድኃኒት ከሌሎች የወባ በሽታ መድኃኒቶች ጋር ሲነጻጸር ፍቱን የሆነ ነው። ምክንያቱም ረቂቆች ሕዋሳትን በፍጥነት ለማጥፋት ችሎታ ስላለው እንዲሁም በጭስ ወይም በሲጋራ መልክ ተዘጋጅቶ በአወሳሰድ በቀላል መንገድ መጠቀም ስለሚቻል ነው።”

ሳይንስና ቴክኖሎጂ

የአገራችን ሳይንቲስቶች ምንም እንኳን በቁጥራቸው ያነሱ ቢሆኑም በራሳቸው ላይ ጠንካራ እምነት እስካላቸው የሌላ ወገኖቻቸውንም ንቃትና ሕሊና መቀስቀስ እንደሚችሉ እምነት አለን። አውሮጳውያን አፍሪቃ ላይ ካደረሱት በደል አንዱ የራሳችን የሆነውን ባህልና ሕብረተሰብ እንድንንቅና በራሳችን እምነት አጥተን ለእነሱ የአእምሮ ባሪያዎች ሆነን እንድንኖር ማድረጋቸው ሲሆን ይህን አጥብቆ መዋጋቱ የኛ ፋንታ ነው። የራሳችንን ዕድገት በራሳችን እንድንወስን “ሰምና ወርቅ” ይህችን አምድ ከፍቷል።