“እንኳን መሞት ማርጀት አለ” (ለምለም ጸጋው)

“አባቶች ሲተርቱ “እንኳን መሞት ማርጀት አለ” ይላሉ። ይህን አነጋገር በተለምዶ ለሚጠቀምበት ሰው ወይንም ሞትን በመጥፎነት ለሚመለከተው ታዛቢ፣ አባቶች ሁለቱን የሰው እድገት ተቃራኒዎችን ያለ አግባብ በማመዛዘን ተችተዋል ብሎ ሒስ ሊያቀርብ ይችላል።”

“ለመላው ዓለም የቀረበ የፊደል ገጸበረከት” (ተክለማርያም ኀይሌ)

“ፊደሎች ጥንት እንደተፈጠሩ በነባርነት ሊኖሩ አይችሉም። ወረታቸው ያልፍና ለዛቸውን ያጣሉ። በዚያን ጊዜ አንዳንድ ታታሪዎች ወይም ደርጅቶች እየተነሱ ክብደታቸውንና አስቸጋሪነታቸውን እየገመገሙ አጣጣላቸውም ሆነ ቅርፃቸው ለጽሕፈት እንዲያመችና ለትምህርት እንዲቀል ማሻሻያ አሳቦችን ያበረክቱላቸዋል።”

“ኪነጥበብ እና ሥነጥበብ” (ይትባረክ ገሠሠ)

“ይህ ጽሑፍ መሠረታዊ ብለን ከምንመድባቸው ጽሑፎች ይመደባል። በተለምዶ የሚሠራባቸውን ቃላት ከትክክለኛው መሠረታቸው (መነሻቸው) ጋር አያይዞ ትክክለኛውን ፍችና ጥቅም እንዲሰጡ ሙከራ ያደርጋል። በተለይም የግዕዝ ቋንቋ ያለውን ጥቅም ለማወቅ ይረዳል ብለን እንገምታለን።”