ስለኢትዮጵያ፡ደራሲያን።

ባ፩ኛው፡ዘመን፡በዐማርኛ፡የተጻፈው፡ሥራ፡ እጅግ፡ጥቂት፡ነው።የተጻፈውም፡ላንዳንድ፡ነገሥታት ምስጋና፡ደራሲው፡ካልታወቀ፡የተገጠመ፡ቅኔ፡ነው። ቅኔውም፡በዘመናት፡ውስጥ፡አንድ፡ቋንቋ፡እንደምን፡ ኹኖ፡እየተለዋወጠ፡ለመኼዱ፡ዋና፡ምስክር፡ከመኾኑ በላይ፣በዚያ፡ዘመን፡የነገሥታቱ፡ሥልጣንና፡የተዘረጋበት፡የሰፊው፡አገር፡ኹኔታ፡እንዴት፡እንደነበረ፣ለታ ሪክና፡ለዦግራፊም፡ማስረጃ፡ለመኾን፡ይረዳል። ዐማርኛው፡ዛሬ፡ዘመን፡የማንናገርበትና፡የማንጽፈው፣ለማስተዋሉም፡የሚያስቸግረንና፡የሰዋስው፡አካኼድ፡የተለዋወጠ፡ብዙ፡ቃልና፡አገባብ፡አለበት። እርሱን፡የመሰለ፡ዐማርኛም፡በየዘመኑ፡እየተጻፈ፡ምናልባት፡እስከ፡ ፲፭፻፺፱-፲፮፻፯፡ደርሶ፡ ይኾናል።

የአቶ ሰይፉ መታፈሪያ የሥነግጥም መድብሎች የጥናት እና የምርምር ሥራዎች ።

ገጣሚ ሲቆጣ (ሰይፉ መታፈሪያ)፣
መጻፍ፣ መጻፍ አለኝ ማቅለም ወረቀት፣ ብእሬን ማስቆጣት ቀይ ደም ማስተፋት።

ዕውቁ ገጣሚ፣ መምህር እና የፎክሎር ባለሙያ ሰይፉ መታፈሪያ ፍሬው በርካታ ያገራችንን እና የአውሮጳን ቋንቋዎች አጥርተው የሚናገሩ እና ጠንቅቀው የሚያውቁ ልሳነ ብዙ ምሁርና ተመራማሪ ናቸው። በኢትዮጵያ እጅግ የተለየ የግጥም አጻጻፍ ስልትን ያስተዋወቁና ያስፋፉ ዕውቅ ገጣሚ ናቸው። እሳቸው እንደሚሉት የግጥማቸው የአጻጻፍ (ዓይነት) „በብዙ ረገድ ባህል-ከተል አይደለም። በዚህ ያጻጻፍ አዲስነት አስገዳጅነትም ስም ስላስፈለገው „ስንኝ አጠፍ ግጥም“ የሚል ስያሜ ሰጥተውታል። ላለፉት ሃምሳ ዓመታት በሀገራችን ቁጥራቸው በርካታ የሆኑ የፎክሎር እና የሥነ ጽሑፍ ተማሪዎችን እና ምሁራንን አፍርተዋል።

አውሮጳ እና ኢትዮጵያ፤ አመራርና የሥልጣኔ ፖለቲካ

በዘመነ መሳፍንት ስድሳ አምስት ዓመት ሙሉ በማይረባ ምክንያት የተከፋፈለውን፣ የዘቀጠውን፣ የባለገውን ህዝባችንን ከወደቀበት መቀመቅ አውጥተው ኢትዮጵያን ወደጥንት ታላቅነቷ ለመመለስ የኢትዮጵያን ነገሥታት፣ መጀመሪያ አፄ ቴዎድሮስ፣ ቀጥሎ አፄ ዮሐንስ በኋላም አፄ ምኒልክ ያውሮጳን መንግሥታት ድጋፍና ወዳጅነት አጥብቀው ይፈልጉ፣ ይማጠኑ ነበር። አውሮጳውያን ግን የሚፈልጉት የኢትዮጵያን ውድቀቷን፣ ክፍፍሏን፣ ንብረቷንና መሬቷን እንጅ የሕዝቧን ነፃነትና ብልጽግና ስላልነበር በነዚህ ቅን ነገሥታቶች ላይ በየጊዜው ተደጋጋሚ አሳፋሪ ሸርና ተንኮል፣ ሴራና ተራ ማጭበርበር ይፈጽሙባቸው ነበር።

መጽሐፈ ምሳሌ ዘጨዋ ተረት  

ይህ መጽሐፍ ያልታተመና በዩናይትድ ስቴትስ የኮንግሬስ ቤተመጻሕፍት ውስጥ በአፍሪካና በመካከለኛው ምሥራቅ ዋና ክፍልየኢትዮጵያና የኤርትራ ሃገራት የመጻሕፍት ክምችት ክፍል ውስጥከሌሎች ካልታተሙ የግእዝ፣ የአማርኛና የትግርኛ መጻሕፍት ጋርይገኛል። የተጻፈው በ1911 ዓ.ም ሲሆን ተረቶቹን በጽሑፍያሰፈረው የንጉሥ ወልደጊዮርጊስ አሽከር ነኝ የሚለው ነጋዴው አቶአበሩ የተባለ  የማጂ ከተማ ነዋሪ ሰው ነው። ይህን ያጠናቀረውንየጥንት ተረት መድብል ለወዳጁ  ለእንግሊዝ መንግሥት መኮንንለሜጀር አጥሒል [Major Athil] ሲያበረክት በመጽሐፉ ላይ ተጽፎእንደተገኘው፣ “ ይህን እያዩ እንዲያስታውሱኝ” ከሚል ማሳሰቢያ ጋርነበር። በዚህ መድብል ውስጥ በወረቀት ላይ ተጽፈው የተገኙተረቶች አስራ ሁለት ያህል ናቸው።

  ‘አኽ፡ሹማዊት ሌሊት፥’                                                         

`አኽ፡ሹም`፥ጥንታዊ፥የ፡`ሳባዊ`፡ሥልጣኔ፡እንደነበራት፡እንጂ፥`ጥንታዊ~ሌሊት`፡እንደ፡አላት፥እስከ፡ዛሬ፡ድረስ፤ፈጽሞ፡ አላውቅም፡ነበር። ብፁዕነታቸው፥ንቡረ~ዕዱ፤የኣጎቴ፡ኣጎት፡ናቸው፥ በብርቱ፥የኅሊና፡ተጽዕኖ፡በሚያሳድር፡ደብዳቤአቸው፥በ፡አጣዳፊ፥ወደ፡`ኣኽ፡ሹም`፡መጥቶ፡እንዲጎበኛቸው፡ስለጠሩት፥ ደብዳቤው፡በደረሰው፡ሠልሥት፥ከ፡ኣሥመራ፡ተነስተን፡የገሠገሥነው።ኣጎቴ፥የ፡ኣሥመራ፡ማዘጋጃ፡ቤት፡ባለ፡ሥልጣን፡ሆኖ፡ከተሾመ፡ቆየ።እኔም፤ለክረምቱ፤የትምህርት፡ቤታችን፡መዘጋት፥ለእረፍት፤ ወደ፡እርሱ፡ዘንድ፡እንድመጣ፡ስለ፡ጠራኝ፤ኣባቴ፤በፍጹም፡ደስታ፤ኣውቶቡስ፡ኣሳፍሮ፡ላከኝ።

የኢትዮጵያ ጊዜያዊ ሁኔታና የመንፈሳዊ ፖለቲካ ራዕይ ከፈንታሁን ጥሩነህ (ዋሺንግተን ዲ.ሲ)

ሰኔ ወር 2010 ዓ.ም ጀምሮ በኢትዮጵያ ምድር የሚካሄደው የለውጥ ነፋስ አዲስና አስገራሚ ነው። በእግዚአብሔር ማመን ተስፋ አስቆርጧቸው የነበሩ ሁሉ ተገርመው የዶክተር አቢይ አህመድ አሊ በፖለቲካው መስክ መነሳት ላይ “የእግዚአብሔር እጅ አለበት” እስኪሉ ድረስ ሁኔታው ማራኪ ሆኖ ይገኛል። በምዕራቡና በምሥራቁ ዓለም የፖለቲካ ንድፈ-ሃሳቦችና ጽንሰ-ሃሳቦች የተራቀቁ ኢትዮጵያውያን ምሁራን በሁኔታው በመደመም የሚሉት አጥተው ዝምታን የመረጡበት ጊዜ ነው። አንዳንድ ዜጎች ደግሞ ይህ ክስተት ጊዜያዊ ቅዠት እንጂ እውን አይደለም በማለት ያላቸውን ግራሞት ይገልጻሉ። እኔ በበኩሌ በዶክተር አህመድ አሊ የሚመራው አዲሱ ፖለቲካ ሲጠበቅ የነበረው የእግዚአብሔር ጣልቃ ገብነት ያስከተለው መሆኑን አምናለሁ። ይህ እምነቴ ደግሞ ይህን መጣጥፍ እንድጽፍ ምክንያት ሆኖኛል።

“የአንድ ኢትዮጵያዊ ደራሲ ሕመም” (እንዳለጌታ ከበደ)

በዚህ ዘመን ያለ አንድ ኢትዮጵያዊ ደራሲ በአብዛኛው ራሱ ጽፎ፣ ራሱ አርሞ፣ ራሱ አስተይቦ፣ ራሱ ፊደል ለቅሞ፣ ራሱ ማተሚያ ቤት ፈልጎ፣ ራሱ አሰራጭቶ፣ ራሱ ማስተዋወቂያ ሠርቶ፣ ራሱ አስመርቆ፣ ራሱ ለኅትመት ያወጣውን ገንዘብ ሰብስቦ፣ … ይኖራል። ብዙ ነው ድካሙ።

መሪራስ አማን በላይ (፲፱፻፵፪-፳፻፱)

በ1997 ዓ.ም ገደማ ከአማን በላይ መተዋወቅ እንደጀመርን በየጊዜው እየተደዋወልን ለረጅም ሰዓቶች በስልክ እናወራ ነበር። ለሀገሩ ሰው ያለውን ሁሉ ዕውቀት የማካፈል ምኞት ስለነበረው አብዛኛውን ጊዜ የሚናገረው እርሱ ነው። እጅግ ሰፊ ትንታኔና ሐተታ ማቅረብ ይችል ነበር።