ፕሮፌሰር ሰይፉ በላይ (1951 – 2019)

ፕሮፌሰር ሰይፉ በላይና እኔ የተዋወቅነው እኔ የሐዋርድ ዩኒቨርሲቲ ተማሪና  የቤተ መጻሕፍቱ ሠራተኛ እያለሁ ነበር። እርሱ በዚያ ጊዜ የሳይንስ ፋክልቲ ተማሪ ነበር። ከተዋወቅን በጥቂት ጊዜ ውስጥ ቀደም ሲል  አውቀው ከነበረው አቶ ሙሉጌታ ከበደ  ጋር  ተቀናጅተን  አንድ  መጽሔት  እንድናቋቁም  ባቀረብኩላቸው ሃሳብ ላይ በመስማማታቸው በውይይት ሰምና ወርቅ ሁለገብ የጥናትና የምርምር መጽሔት በሚል ርእስ መጽሔት የማቋቋሙንና  በተግባር የመግለጹን እርምጃ   ተያያዝነው። እኔ የመጽሔቱ ዋና አዘጋጅ እንድሆን፣  ፕሮፌሰር ሰይፉና አቶ ሙሉጌታ ደግሞ የአዘጋጅው ቦርድ አባላት በመሆን አብረውኝ ሊሰሩ ተስማማን። የመጀመሪያውን እትም በምናዘጋጅበት ጊዜ እንደስምምነታችን በሁሉም የእውቀት ዘርፍ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን ያሉበትን ደረጃ በመገምገም እንድንጀምር የሚል ሃሳብ ስለነበረ ፕሮፌሰር ሰይፉ በሳይንስና ቴክኖሎጂ ያለውን ድርሻ በሚገባ ሰርቶ አቅርቦልናል። ከዚህም የመንደርደሪያ ጥራዝ በኋላ ፕሮፌሰር ሰይፉ በላይ በቀጣዩ ጥራዝ ላይ ማለትም ጥር 1979 . በታተመው እትም ላይ የፕላስቲክ ኪነ ጥበብ” በሚል ርእስ ላይ ሰርቷል፤  ሰኔ 1979 . በታተመው ላይ ደግሞ ጥንታዊ የብረት ቴክኖሎጂ በኢትዮጵያ” በሚል ርእስ አንድ መልካም ጽሑፍ ለአንባቢያን አቅርቧል። በመጨረሻም የኢትዮጵያውያን የሳይንስ ሙያተኞች ድርጅት” በሚል አንድ ተጨማሪ ጽሑፍ ጥር 1981 . በወጣው እትም ላይ አቅርቧል።

ፕሮፌሰር ሰይፉ በላይ ከሐዋርድ ዩኒቨርሲቲ በባዮቴክኖሎጂ ከፍተኛ ድግሪ ከተቀበለ በኋላ፥   በአሜሪካ መንግስት መሥሪያ ቤቶች (በዋልተር ሪድስና ኤን አይ ኤች – Walter Reed Medical Center & NIH) እንዲሁም  በግል የምርምር ኩባንያዎች (ኤስ አር ኤል ላይፍ ሳይንስና ባዮቲስኩዌር – SRL Life Sciences & Bio-T Square LLC) ውስጥ በዋና ሥራ አስኪያጅነትና ተመራማሪ ሳይንቲስትነት ከሰላሳ አምስት ዓመቶች በላይ ሠርቷል። በተጨማሪም የቻርለስ ፓርከር ተሸላሚ ከመሆኑ በላይ፥ በተለያዩ ግኝቶቹ ውጤታማነት የፈጠራ መብት (ፓተንት) ባለቤትም ነው። የጥናቱ ትኩረት በህብረ ህዋስ (Tissue) ደረጃ በግብርናና ጤና ዙርያ ያጠነጠነ ሲሆን፥ ከሚጠቀሱት ጥናቶች መካከል የጤፍን ምርታማነት ማሳደግ፥ የቬርኖንያና፥ እንደ ኤድስ ላሉ የቫይረስ በሽታዎች የመከላከያና የሕክምና ዜዴዎችን መፍጠር ይገኛሉ።   

ወደኢትዮጵያ በመግባት በአሜሪካ ሃገር የተማረውን ትምህርት በሃገሩ በኢትዮጵያ በተለይም ከኢትዮጵያ የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር  ሥራ  ላይ  ለማዋል  በነበረው  ህልም  መልካም  ውጤት  አስመዝግቧል።  የዚህ  ዓላማው  ውጤት በኢትዮጵያ የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት መዛግብት ውስጥ ተመዝግቦ  አግኝተናል፤ ” ለበርካታ ዓመታት በአሜሪካ ሀገር ልዩ ልዩ የምርምር ፕሮጀክቶችን በመስራት ከፍተኛ ልምድ ያካበቱት የባዮ ስኩዌር የጥናትና የምርምር ድርጅት ዋና ዳይሬክተር / ሰይፉ በላይ  በኢትዮጵያ  ኢኮኖሚ  ላይ  አዎንታዊ  ለውጥ  ያመጣሉ ያሏቸውን አስር የሚሆኑ የምርምር ፕሮጀክቶችን አቅርበዋል።” 

Screen Shot 2020-01-18 at 6.25.45 PM.pngScreen Shot 2020-01-18 at 6.24.27 PM.png

ፕሮፌሰር በላይ ከባልቤቱና ከልጁ ጋር                                              ፕሮፌሰር ሰይፉ ከባልቤቱና ከአባቱ ጋር

ባጠቃላይ ፕሮፌሰር ሰይፉ ጠባየ ሸጋ ነበረ፤ በቁም ነገርም ሆነ በቧልት ጊዜ ምን ጊዜም ደስ የሚል ፈገግታ አይለየውም ነበር። ምንም እንኳ ከሃገሩ የወጣው ለረጅም ዓመት ቢሆንም የሀገር ፍቅር ስሜቱ ከፍተኛ ስለነበረ ትምህርቱን ጨርሶ ከተመረቀ በኋላ ለረጅም ጊዜ በዩናይትድ ስቴትስ በተለይ ለኤይድስ በሽታ መድኃኒት ለማግኘት ጥረት በሚደረግበት ተቋም ተቀጥሮ ይሰራ እንደነበር አስታውሳለሁ። በአሜሪካ ያደለበውን እውቀት ይዞ ሊሰራበት ወደኢትዮጵያ በመመለስ ጥቂት ዓመታት ከሰራ በኋላ ታሞ በስድሳ ስምንት ዓመቱ በሞት መለየቱን ሰማን።

በበጎ ፈቃድ ተነሳስቶ ለሃገሩና ለኢትዮጵያ ህዝብ ባደረገው አስተዋጽ እስከመጨረሻው ሲታወስ ይኖራል። 

ለውድ ልጁ፣ ለውድ ባለቤቱና  ለወንድሞቹና ለመላ  ቤተሰቡ  እግዚአብሔር  መጽናናትን  እንዲሰጣቸውና  እንዲያጠነክራቸው  የሰምና ወርቅ መጽሔት አዘጋጂዎች ጥልቅ የሆነ ሃዘናቸውንና መልካም ምኞታቸውን ይገልጻሉ።

የውንድማችን ነፍስ ከፈጣሪ አምላክ አጠገብ እንዳትለይ ፀሎታችን ነው

በሰምና ወርቅ መጽሔት አዘጋጆች ስም

ፈንታሁን ጥሩነህ

4 thoughts on “ፕሮፌሰር ሰይፉ በላይ (1951 – 2019)

  1. Thank you very much for sending me this information and the first copy of
    Semna Worq Magazine. I know there have been promises I was given many times
    in the past. Today, that promise proved to be kept by my friend, FT.
    Amesegnallehu!

    kg

    Liked by 1 person

    • ዶ/ር ከበደ እንደምን አለህ፤
      መጽሔቱን አንብበህ አስተያየት በመስጠትህ ደስ ብሎኛል፡፡ እንደተነጋገርነው ጽሑፍ ጽፈህ እንድትልክልን አደራ፣ ካንተ ብዙ ስለምንጠብቅ፡፡
      በተረፈ በሰላም ያገናኘን።
      ፈንታሁን

      Like

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.