ዶክተር ማይገነት ሺፈራው ሰምና ወርቅ የጥናትና የምርምር መጽሔት የመጀመሪያ እትሙን ለማውጣት ዝግጅት በሚያደርግበት ጊዜ የሙያዋ ክፍል በሆነው ትምሕርት አንጻር አንድ መጣጥፍ አዘጋጅታ አበርክታለች። ይህ ጽሑፍ በኢትዮጵያ ውስጥ እስከ 1980 ዓ.ም. የነበረውን የትምሕርት ሥርዓትና አሠጣጥ የሚገመግምና የሚዳስስ ጠቃሚ ጽሑፍ ነበር። በሰምና ወርቅ መጽሔት አባልነትም አብራን ቆይታለች። የዶክተር ማይገነትን ነፍስ ከአብርሃምና ከሳራ ከጻድቃን ጋር ያኑርልን።